በትግራይ የሚገኙ የፌድራል ፖሊስ አባላት አሁንም ምላሽ አላገኘንም አሉ፡፡

የትግራይ ተወላጅ የፌድራል ፖሊስ አባላት በተሃድሶ ስልጠና ተስጥቷቸው ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ ደብዳቤ ቢደርሳቸውም ምላሽ አላገኘንም ብለዋል።

መንግስት አሁኑ ክፍያ እንደሚፈፀምና በተሃድሶ ሰልጥነው ወደ ስራ እዲመለሱ ደብዳቤ ቢወጣም ይሁን እንጂ በክልሉ ካሉ ከ7 መቶ በላይ አባላት አንዳቸው እንዳልተከፈላቸው ለጣቢያችን ተናግረዋል።

በክልሉ የአባላቱ ተወካይ ዋና ሳጅን መብራቱ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ወደ ስራ ገበታቸው እንዲመለሱ የተደረጉት በሰሜኑ ጦርነቱ ወቅት ከትግራይ ውጭ የነበሩና መኖራቸውንም በአካል ያሳወቁ ናቸው ብለዋል።

እኛ መኖራችንን ለማሳወቅ ብዙ ርቀት ብንጓዝም ችላ ተብለናል ብለዋል።
በተሃድሶ ስልጠና ወደስራ ገበታቸው እንዲመለሱ የተደረጉ አባላት ቢኖርም መንግስት የእኛንም ጉዳይ ተመልክቶ ተገቢ ምላሽ ይስጠን ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል።

ከዚህ ቀደም ከ7 መቶ በላይ የፌድራል ፖሊስ አባላት ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው የመቀሌ ቅርንጫፍ እንባ ጠባቂ ተቋምን ጠቅሶ ጣቢያችን መዘገቡ የሚታወስ ነው።

በለአለም አሰፋ

ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply