በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር የተቋቋመው የአማካሪ ምክር ቤት ጥያቄ ተነሳበት፡፡

በቅርቡ ያቋቋመው ይህ የአማካሪ ምክር ቤት አብዛኛው ቦታ በህውሃት አባላት የተሞላ ነው ሲል ሳልሳይ ወያኔ ትግራይ ከሷል፡፡

የሳልሳይ ወያኔ ትግራይ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት አቶ ኪሮስ ሃይለስላሴ ከጣብያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ ለአማካሪ ምክር ቤቱ የተመረጡ አካላት በአብዛኛው የህውሃት አባላትና ደጋፊዎች ናቸው ብለዋል፡፡

ለይስሙላ ከተመረጡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በስተቀር በአብዛኛው በህውሃት ሰዎች የተያዘ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

ከዛም ባለፈ ከአማካሪ ምክር ቤት ይልቅ ግዚያዊ ምክር ቤት መቋቋም ነው ያለበት ብለን ብንጠይቅም ሰሚ አጥተናል ነው ያሉት፡፡

ግዚያዊ መንግስቱ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በዚህ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ሲያደርጉ መቆየታቸውን የሚናገሩት አቶ ኪሮስ ይሁን እንጂ ግዚያዊ መንግስቱ በመጨረሻ የራሱን ውሳኔ ወስኗል ብለዋል፡፡

ስለሆነም ሳልሳይ ወያኔ ትግራይን ጨምሮ አረና ትግራይ ሉአለዊነት ዴሞክራሲ ፣ እንዲሁም አሲምባ ዴሞክራስያዊ ፖርቲ እራሳቸውን ከአማካሪ ምክር ቤቱ ማግለላቸውን አስታውቀዋል፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሥራዎቹን የሚቆጣጠርለት የአማካሪ ምክር ቤት እንዲቋቋም ወስኖ የመመሥረቻ ደንቡን ማፅደቁ ይታወሳል፡፡

አቤል ደጀኔ

መጋቢት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply