በትግራይ 92 የምግብ ማሰራጫ ማዕከላት መቋቋሙ ተገለጸ።

በትግራይ ክልል ለ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎችን እርዳታ ለመስጠት ዝግጅት መደረጉም ተገልጿል።

በትግራይ ህግ ከማሰከበር ዘመቻ በፊት 1.8 ሚሊየን ዜጎች እርዳታ የሚፈልጉ ነበሩ።

የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ እና በቤንሻጉል ጉምዝ መተከል ዞን በክልሉ ስላለው የሰብዓዊ ዕርዳታ ለዜጎች ለማድረስ የሚደረግ እንቅስቃሴ እና አጠቃላይ በተመለከተ መግለጫ እየሰጡ ነው።

የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ የማቋቋም እና ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ያልሆነ ድጋፍ በቅንጅት እየተሰራ ነው።

በመቀሌ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ማስተባበሪያ ተቋቁሟል በትግራይ 92 ምግብ ማሰራጫ ጣቢያ አለ።

አጠቃላይ የሰብዓዊ የረድኤት ተቋማትን ጨምሮ ሁሉም አካላት ስራቸውን ከፌደራል መንግስት ጋር ተቀናጅተው እንዲያከናውኑ እና ከውጭ ድርጅቶችም ጋር እየተሰራ ነውም ተብሏል።

በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች በትግራይ ክልል 4.5 ሚሊየን እርዳታ የሚፈልግ ዜጋ አለ እያሉ የሚለቁት መረጃዎች በፌዴራል መንግስት ያልጸደቀ ቁጥር እንደሆነም በመግለጫው።

በዳንኤል መላኩ
ጥር 13 ቀን 2013 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply