“በቻልነው ሀቅም ሁሉ ከህዝባችን ጎን ነን!” አቶ ወርቁ አይተነው! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 2 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ባለሃብቱ አቶ ወርቁ አይ…

“በቻልነው ሀቅም ሁሉ ከህዝባችን ጎን ነን!” አቶ ወርቁ አይተነው! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ታህሳስ 2 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ባለሃብቱ አቶ ወርቁ አይተነው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል:_ አሁን ያለንብት ስአት የመተሳሰብ የመረዳዳትና ለተቸገረው ወገናችን የመድረስ ግዴታችን እምናሳይበት ወቅት መሆኑን በመረዳት ላለፋት 3 ቀናቶች ወደ ቤንሻንጉል ክልል አምርቻለሁ። ለመጭው 3 ወር እንዲደርስ እና ለምወደው ለማከብረው በጦርነቱ ለተፈናቀለው ብሎም በጦርነቱ ምክንያት ህውኃት ሀብት ንብረታቸውን ዘርፋ ባዶ ቤት ላረገችው ማህበረሰብ የቻልኩትን ያክል ለማገዝ እንዲሁም መልሶ መቋቋሙ በተቻለው መጠንም እንዲፈጥን ለማረግ እራሴ በአካል በመገኘት እንደ ቆላ ስንዴ እና ሌሎች ተዛማች የሆኑ የእህል አቅርቦት ለወገኔ በፍጥነት ለማድረስ በሞቀታማው በርሀ እርሻ ቦታ ተገኝቸ ሁኔታወችን እያስተባበርኩ እገኛለሁ። እኛ ኢትዮጵያውያን የመረዳዳት እና የመተሳሰብ ባህላችንን ከቅድመ አያቶቻችን እንደወረስነው ሁሉ ሁላችንም በተሰማራንበት መስክ 1 ለራሴ 3 ለተጎዳው ወገኔ የሚለውን እሳቤ በህሊናችን ውስጥ በማስገባት ይህን መጥፎ ግዜ በመተባበርና በመረዳዳት ከወገናችን ጎን እንሁን እላለሁ። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Source: Link to the Post

Leave a Reply