በቻምፒየንስ ሊጉ ፖርቶ እና ዶርትመንድ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት ተደርገዋል፡፡

በምሽቱ ጨዋታ ወደ ፖርቹጋል ያቀናው ጁቬንቱስ በፖርቶ 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡

ታሬሚ እና ማሬጋ ለፖርቶ የድል ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ ኪዬዛ ጁቬንቱስ ለመልሱ ጨዋታ ተስፋ የሰነቀባትን ማስተዛዘኛ ጎል አስቆጥሯል፡፡

በሌላኛው የምሽቱ ጨዋታ ደግሞ በሜዳው ቦሩሲያ ዶርትመንድን ያስተናገደው ሴቪያ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

ሴቪያ በፈርናንዴዝ ሳኤዝ ጎል ቀዳሚ ቢሆንም ዶርትመንድ በሃላንድ ሁለት ጎሎች እና ዳሁድ 1 ጎል ጨዋታውን 3 ለ 1 መምራት ችሏል፡፡

ደ ዮንግ ለባለሜዳዎቹ በጨዋታው መጠናቀቂያ ከሽንፈት ያልታደገቻቸውን ጎል አስቆጥሮ ጨዋታው 3 ለ 2 ተጠናቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በቻምፒየንስ ሊጉ ፖርቶ እና ዶርትመንድ ድል ቀንቷቸዋል appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply