በቻይናው ርዕደ መሬት አደጋ የተሰወሩትን ሰዎች ማፈላለግ ቀጥሏል

https://gdb.voanews.com/00e90000-0aff-0242-e7d6-08da9042956b_w800_h450.jpg

ቻይና ውስጥ ባላፈው ሰኞ ከደረሰው የርዕደ መሬት አደጋ ጋር በተያያዘ የተሰወሩትን 26 ሰዎች የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ማፈላለግ የያዙ መሆኑ ሲነገር ቢያንስ 74 የሚሆኑን ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

የቻይና መንግሥት ዜና ማሰራጫ የሆነው ሲሲቲቪ እንደዘገበው በሬክተል ስኬል 6.8 በሆነው የርዕደ መሬት አደጋ መውጫ አጥተው የቀሩ በርካታ ሰዎችን የአደጋ ጊዜ ሠራተኞቹን እያፈላለጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከአደጋው ጋር ተያይዞ በደቡባዊ ምስራቅ ቻይና ሲሿን ክፍለ ግዛት፣ ሉዲንግ በተባለው ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት 300 የሚደርሱ ነዋሪዎች ወደ ሌላ ቦታ የሰፈሩ ሲሆን ከመካከላቸው 29 የሚሆኑት የቆሰሉ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

ርዕደ መሬቱ ከደረሰበት ስፍራ፣ 200 ኪሎ ሜትሮች ርቀት በምትገኘው የክፍለ ግዛቲቱ ዋና ከተማ ድረሰ ዘልቆ መሰማቱም በዘገባው ተመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply