በቻይና እና አሜሪካ የተሳሳተ ግጭት ስጋት ዉስጥ ገብቻለሁ ስትል ሲንጋፖር ገለጸች፡፡በቅርቡ መቋጫ የሚያገኝ በማይመስለዉ በታይዋን ላይ ባንዣበበዉ የቻይና- አሜሪካ ዉጥረት ስጋት ላይ መዉደቃቸ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/kkMTOhRY4yHqJOEmWRLRX46_vgjkU4l1XtZBfgbeTypnWwPelJakiyXY7UaZFR52ShG0YzBo4WGk6VnkMcnBKEN4cHjRh5QS2i6wgMm4VqUa97eIgcM-awIDSZ-8Z5wGkBfiiL8xSEyW8gqCdopD7grXWjkuyUSzXtmQFlFjGtd-TF-_C66C5FATm1wx7Tj3AB7tE1N1Ffnz443MtH5kisAxZ15KPk3Y-ZR7VqkCzUGX1Wfy3yWKHTiHXAZidJLMo3cdJ72HXaNnAlVh9Doffo5FGPDVTPa1pQQ5qpcLyw2Hr6d_xm9A9m_bl_ePBqoP2pgnpuwcOskkaeoP-DbgLg.jpg

በቻይና እና አሜሪካ የተሳሳተ ግጭት ስጋት ዉስጥ ገብቻለሁ ስትል ሲንጋፖር ገለጸች፡፡

በቅርቡ መቋጫ የሚያገኝ በማይመስለዉ በታይዋን ላይ ባንዣበበዉ የቻይና- አሜሪካ ዉጥረት ስጋት ላይ መዉደቃቸዉን የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስቴር ገልጸዋል፡፡

በክልሉ ባለዉ ዉጥረት እና ፉክክር ሲንጋፖር መደቆሷ እንደማይቀር ያላቸዉን ስጋት በመግለጽ፣ ሀገሪቱ አሁን ካላት መረጋጋት እና ሰላም በተለየ መልኩ እራሷን ማዘጋጀት እንዳለባትም ተናግረዋል፡፡

ጥልቅ ጥርጣሬ እንዲሁም የማያልቅ የሚመስል ፉክክር በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለዉን ግንኙነት የበለጠ እያሻከረዉ መጥቷል፡፡ አከባቢዉም ስጋት ከቦታል ››ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩ በቅርቡ የሚቋጭ አይመስልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ፣ አንድ ትንሽ ስህተት ጉዳዩን የበለጠ ልታወሳስበዉ እና አደጋዉንም ከፍ ልታደርገዉ እንደምትችል ያላቸዉን ስጋት አብራተዋል፡፡

አለም በቅርቡ ወደ ተለመደዉ ዝቅተኛ የዋጋ ግሽበት እና የተስተካከለ ኑሮ እንደማትመለስ እርግጠኛ ነኝ ሲሉ ያላቸዉን ስጋት መግለጻቸዉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ሐምሌ 03 ቀን 2014 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።

ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply