በነቀምቴ ከተማ አራት የአባቶርቤ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ፖሊስ ገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥቅምት 14 ቀን 2013 ዓ.ም       አዲስ አበባ ሸዋ በነቀምቴ ከተማ አራት…

በነቀምቴ ከተማ አራት የአባቶርቤ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ፖሊስ ገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በነቀምቴ ከተማ አራት…

በነቀምቴ ከተማ አራት የአባቶርቤ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ፖሊስ ገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በነቀምቴ ከተማ አራት የአባቶርቤ አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን የከተማው ልዩ ፖሊስ ገልጿል፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ሊገደሉ የቻሉት በነቀምቴ ከተማ ውስጥ አባቶርቤ በሚል ስም በተለያዩ ጊዜያት የሰዎችን ሕይወት በማጥፋት ተጠርጥረው ጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 5:30 ቀሶ ተብሎ በሚታወቀው ቦታ ላይ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ለማዋል ባደረገው ጥረት ፖሊስ ላይ ተኩስ በመክፈታቸው መሆኑን የነቀምቴ ከተማ የልዩ ኃይል ኃላፊ ኮማንደር ግርማ አብዲሳ ገልጸዋል፡፡ በእነዚህ ግለሰቦች ላይ በተወሰደው እርምጃ ጋር ተያይዞ ሁለት ቦምብ፣ ሶስት ሽጉጦች፣ ድምጽ አልባ የጦር መሳሪያዎችና የቀድሞ የአገር መከላከያ ሰራዊት አልባሳት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮማንደር ግርማ ገልጸዋል፡፡ ኮማንደር ግርማ በግለሰቦቹ ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ህብረተሰቡ ያደረገውን ትብብር አድንቀው፣ በህብረተሰቡ ውስጥ ተደብቀው ያሉት የእነዚህ አካላት ርዝራዦችን በማጋለጥ ረገድ ህብረተሰቡ የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ኦቢኤን ስለመዘገቡ ጠቅሶ ኢቢሲ በገጹ ላይ አስፍሯል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply