በነቢይ መኮንን ድንገተኛ ህልፈት ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶናል!!

በነቢይ መኮንን ድንገተኛ ህልፈት ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶናል!!

ከአዲስ አድማስ  መሥራቾች አንዱ የሆነውና በዋና አዘጋጅነት ጋዜጣዋን በመምራት ተወዳጅ ካደረጓት በቀዳሚነት የሚጠቀሰው ገጣሚ፣ ተርጓሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን፣ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ስንገልጽ፣ በጥልቅ ሃዘን ውስጥ ሆነን ነው፡፡

 ገጣሚና ደራሲ ነቢይ መኮንን ባደረበት ህመም ህክምና ሲከታተል ቆይቶ፣ ድንገት ያረፈው ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም  ረፋዱ ላይ ነው፡፡

የአዲስ አድማስ ዝግጅት ክፍል፣ የጋዜጣው መሥራችና ዋና አዘጋጅ በነበረው ነቢይ መኮንን ድንገተኛ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለጸ፤ ለቤተሰቦቹ፣ ወዳጆቹና አድናቂዎቹ መጽናናትን ከልብ ይመኛል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply