በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ በጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አስታወ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/FO-pQOYnvYFk9TCmqI1etWSGmc298ivpm4vlSmKgyZjgdMJyEA2EwMKst1M_adp0XvAfdN_wQz9ojGqRay9Qyrp7uLZrnVYmo0ck3suhwmgtlKe-OnHJWrGxky8_-d6XxjstLWzC7c3uNb2yixLMZDTg40s-L7OLNvkTc4dj8_MzC_EZzfduL1HgCwFBnDwlVOBRO5KjlmpItcuHJV0fU3nTr74OUig8x9B3kKiUe76ctwtcXRgwqopN5zLEF7rVQI1yAqPQshUNkHpYkKHErZfpu1tPRLLziAnR6xeCZ98yH5HOPOduQr1DGh0AATe4nZidYXLDi0adZVxHelpAlg.jpg

በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ

በጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ፣ ከዛሬ ታኅሣሥ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ የሚሆን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ክለሳ መደረጉን ገልጿል።

በዚሁ መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ፦

ቤንዚን በሊትር – 61 ብር ከ29 ሣንቲም

ነጭ ናፍጣ በሊትር – 67 ብር ከ30 ሣንቲም

ኬሮሲን በሊትር – 67 ብር ከ30 ሣንቲም

ቀላል ጥቁር ናፍጣ – 49 ብር ከ67 ሣንቲም

ከባድ ጥቁር ናፍጣ – 48 ብር ከ70 ሣንቲም

የአውሮፕላን ነዳጅ – 67 ብር ከ91 ሣንቲም መሆኑን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስቴር ገልጿል።

የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ በሚመለከት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሕዝብ ማስታወቂያ እንዳዘጋጀ እና በዚሁ የሕዝብ ማስታወቂያ የተካተቱ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዝርዝር ከነገው ዕለት (ጥር 01 ቀን 2015 ዓ.ም) ጀምሮ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ማደያዎች ሁሉ ተግባራዊ እንደሚሆን ገልጿል።

መንግሥት ያወጣው የታለመለት የድጎማ ሥርዓት አፈፃፀም ላይ አንዳንድ ሊስተካከሉ የሚገባቸው ክፍተቶች ቢኖሩትም ከጥር ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ በሚደረገው የዋጋ ክለሳ፣ ዝቅተኛ ገቢ ላለው ኅብረተሰብ የሚሰጠው ድጎማ እንዲጨምር መደረጉን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ገልጿል።

በዚሁ መሠረት በአንድ ሊትር ቤንዚን ሲሰጥ የነበረው ድጎማ ከብር 15.76 ወደ ብር 17.33 እንዲሁም የአንድ ሊትር ናፍጣ ድጎማ ከብር 19.02 ወደ ብር 22.68 ከፍ እንዲል መደረጉ ተገልጿል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply