በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ ሙሉ በሙሉ አለመከልከሉን ገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ዶ/ር ዓለሙ ስሜ ለፓርላማው የከተማ መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ሲያቀርቡ፣ በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ አውቶሞቢሎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ውሳኔ መተላለፉን መናገራቸው ይታወሳል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሕግ አማካሪ አቶ ዋሲሁን አባተ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች አገር ውስጥ እንዳደይገቡ በመከልከል የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ብቻ እንዲገቡ የሚፈቅድ ምንም ዓይነት መመሪያም ሆነ ውሳኔ የለም ብለዋል፡፡

በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል እየተከናወነ ያለው ሥራ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ ለማበረታታትና በነዳጅ የሚሠሩት ደግሞ በብዛት እንዳይገቡ ተስፋ ለማስቆረጥ፣ የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ የተደነገገበት ሁኔታ መኖሩን አቶ ዋሲሁን ተናግረዋል፡፡

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ማገድ በዓለም የንግድ ድርጅት ሕግ መሠረት የማይቻል በመሆኑ፣ የአገሪቱን የቀረጥ ሥርዓት በመጠቀም ኢኮኖሚ ለማሳደግ የሚጠቅሙትን ማበረታት፣ ጎጂ የሆኑትን ደግሞ እንዳይስፋፉ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥር 22 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply