በነዳጅ የሚሰሩ የቤት አውቶሞቢሎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ክልከላ ተደረገ፡፡

ከሌሎች በተለየ መልኩ ወደ ሃገር እንዳይገቡ የተከለከሉት በነዳጅ የሚስሩ የግል አውቶሞቢሎች ናቸው ተብሏል።

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የህዝብ ትራንስፖርት እና አሽከርካሪ ተሸከርካሪ መሪ ስራ አስፈጻሚ ተወካይ አቶ አበራ ሞሲሳ፤ አውቶሞቢሎች በሃገር ውስጥ በመብዛታቸ ምክንያት በሃገራችን ኢኮኖሚ ለነዳጅ የሚወጣውን ወደ ኤሌክትሪክ ቢቀየር የበጀት የውጭ ምንዛሬ ስለሚቀንስ እሱን ታሳቢ ተደርጎ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በኤሌክትሪክ የሚሰሩ አውቶሞቢሎች የአየር ብክለት ከመቀነስ አንጻር ከፍተኛ ሚና ስለሚኖራቸው የቤት አውቶቢሎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ክልከላ ለመጣል ምክንያት ከሆኑ መካከል ይገኙበታል ብለዋል።

አሁን ባለው ደረጃ እንደመጀምሪያ ተግባራዊ የተደረገው የቤት አውቶሞቢሎች ላይ ብቻ መሆኑን እና ወደ ፊት ግን ሌሎች ተሽከርካሪዎች ላይ ተግባራዊነቱ እንደሚቀጥል አቶ አበራ አስረድተዋል፡፡

ይህ ክልከላ ባለው የኢኮኖሚ እና የአየር ንብረት ጋር ተያይዞ የአየር ብክለቱን ለመቀነስ ታስቦ ተግባራዊ መደረጉን ህዝቡ መገንዘብ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው

ጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply