በነገው ዕለት ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ 

ቅዳሜ ሰኔ 22 ቅን 2016 (አዲስ ማለዳ) መቻል ስፖርት ክለብ “መቻል ለኢትዮጵያ ” በሚል መሪ ቃል 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን እያከበረ ይገኛል።

ምስረታውን አስመልክቶ ነገ ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በአዲስ አበባ ከተማ መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ አድርጎ ይካሄዳል።

ሩጫው የአዲስ አበባ ዋና ዋና መንገዶችን የሚያካልል ሲሆን፡-

. ከብሔራዊ ቤተመንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ

. ከካዛንቺስ ወደ ባምቢስ

. ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ

. ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት

.ከለገሃር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ

. ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ

የሚገኙ መንገዶች ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ሩጫው እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ አንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply