በነገው ዕለት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርኃ ግብር ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ***በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚካሄደው የአደባባይ…

በነገው ዕለት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርኃ ግብር ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ
***

በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚካሄደው የአደባባይ ላይ የኢፍጣር ፕሮግራም በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ  ግብረ-ሐይሉ አስታወቀ፡፡

በነገው ዕለት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርኃ ግብር  ጋር ተያይዞ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡

በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚካሄደው የአደባባይ ላይ የኢፍጣር ፕሮግራም በሰላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የፀጥታና ደህንነት የጋራ  ግብረ-ሐይሉ አስታውቆ በፕሮግራሙ አከባበር ዙሪያ ከእምነቱ አባቶችና ከወጣት በጎ ፈቃደኞች ጋር ተገቢውን ውይይት በማድረግ ዝግጅት መደረጉንም ግብረ-ሐይሉ ገልጿል፡፡

የእምነቱ ተከታዮች ወደ ኢፍጣር ፕሮግራሙ ሲመጡ ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ መኖሩን ተረድተው እንደወትሮው ሁሉ ትብብር እንዲያደርጉ የተጠየቀ ሲሆን ከፕሮግራሙ ጋር የማይሔዱ በህግ የተከለከሉ እና ስለታማ ነገሮችን ይዞ መምጣት ፈፅሞ ክልክል መሆኑን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ሐይሉ አስታውቋል፡፡

በነገው ዕለት መጋቢት 18 ቀን 2016ዓ.ም በአዲስ አበባ ከሚካሄደው ታላቁ የኢፍጣር መርኃ ግብር ጋር ተያይዞ ከ5፡00 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
•  ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅ/ኡራኤል ቤ/ክርስቲያን

•  ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ   ኦሎምፒያ

•  ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ለከባድ መኪናዎች አጎና ሲኒማ፤ ለሌሎች ተሸከርካሪዎች ጥላሁን አደባባይ ጋር ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡

•   ከጦር ኃይሎች በሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሸከርካሪዎች  በተለምዶ አጠራሩ ክቡ ባንክ አካባቢ፡፡

•  ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሐራምቤ መብራት ላይ፡፡

• እንዲሁም ከ4 ኪሎ በውጭ ጉዳይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ብሔራዊ ቤተ መንግስት መስቀለኛው ላይ፡፡

•   ከአዋሬ አካባቢ በካሳንቺስ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ኢንተርኮንትኔታል አካባቢ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢፍጠር ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅበት ሰዓት ድረስ ዝግ የሚደረጉ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም በተገለፁት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓታት ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ ሲሆን ኅብረተሰቡ መርኃ ግብሩ በሠላም ተጀምሮ በሠላም እንዲጠናቀቅ ለፀጥታ አካላት ተባባሪ እንዲሆንና ማንኛውም ዓይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በፖሊስ የመረጃ ስልኮች 0111 11 01 11 እና ነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወልና መረጃ በመስጠት የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ የፀጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply