You are currently viewing በኒውዝላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በአማራ ላይ የሚፈፀመውን መንግስት መር የዘር ፍጅት የሚያወግዝ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ሊያካሂዱ መሆኑ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ግንቦት 2…

በኒውዝላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በአማራ ላይ የሚፈፀመውን መንግስት መር የዘር ፍጅት የሚያወግዝ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ሊያካሂዱ መሆኑ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 2…

በኒውዝላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በአማራ ላይ የሚፈፀመውን መንግስት መር የዘር ፍጅት የሚያወግዝ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ሊያካሂዱ መሆኑ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 2 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የኒውዝላንድ መንግስት መቀመጫ ከሆነችው ከዌልንግተን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል በሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው በኢትዮጵያ በአማራ ህዝብ ላይ በተከታታይ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በመንግስት መዋቅሩ ውስጥ በተሰገሰጉ አካላት ድጋፍ እየተፈፀመ ያለውን የጅምላ ፍጅት የሚያወግዙበት ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ያመለክታል። ሰላማዊ ሰልፉ የሚደረገው በዌሊንግተን ከተማ ነገ ሜይ 11 ቀን 2021፣ 10 AM ላይ ሲሆን በኒውዝላንድ የሚኖሩ የዘር ፍጅትን የሚቃወሙ አማራዎችን ጨምሮ ሌሎች ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንም እንደሚገኙበት ተጠቁሟል። በኒውዝላንድ ዌሊንግተን የሚካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ የአስተባባሪ ኮሚቴው አባል የሆኑት አቶ ፈንታሁን ወርቁ የዘወትር የአማራ ሚዲያ ተከታታይ መሆናቸውን በመግለፅ የሚዲያ ሽፋን እንዲሰጣቸው እንደሚፈልጉ ቀድመው ጠይቀዋል። በሀገር ግንባታው ረገድ ታላቅ አበርክቶት ያለው የአማራ ህዝብ በጽንፈኛ፣ተስፋፊና የአሸባሪ ቡድን አባላት በየጊዜው የዘር ፍጅት ሲፈፀምበት መታደግ ያልቻለውና የዘር ማጥፋት ነው ብሎ ለመጥራት የሚሽኮረመመው መንግስት በዝምታ እየተባበረ ብቻ ሳይሆን በመዋቅሩ ውስጥ ተሰግስገው ለገዳዮች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ስንቅና ትጥቅ እያቀበሉ፣ ጥላቻ እና መለያየትን እየሰበኩ የሚውሉ በርካታ ካድሪዎችን አላፀዳም ከማለታቸው ባሻገር ሌሎች ማሳያዎችን በመጥቀስ ጥቃቱ መንግስት መር ነው ሲሉ ይደመጣሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply