በናይጄሪያ የቦኮ-ሃራም አሸባሪ ኃይሎች ካገቷቸው ተማሪዎች 17 ያህሉን መታደግ ተችሏል፡፡

በቦኮ-ሃራም አሸባሪ ኃይሎች ከተያዙት በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች መካከል የሁለት ተማሪዎች ህይወት ማለፉና ሌሎች ከ600 በላይ ተማሪዎችንም ከአሸባሪዎቹ እጅ ለማስለቀቅ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ተብሏል፡፡

የናይጄሪያ የመንግሥት ባለስልጣናት በሰጡት ማብራሪያ በሰሜናዊ ምዕራብ ናይጄሪያ ከትምህርት ቤት የታገቱ 17 ተማሪዎችን ማስለቀቅ ተችሏል፡፡የከትሲና ግዛት አስተዳዳሪ አሚኑ ማሣሪ ለሀገሪቱ ሬድዮ እንደተናገሩ በካንካራ ትምህርት ቤት ያሉ ተማሪዎች ከታገቱ በኋላ የሀገሪቱ ጦር አሸባሪዎቹን የገቡበት ገብቶ እንዲመነጥርና የተያዙትን ተማሪዎች እንዲያስለቅቅ ትዕዛዝ ሰጥቻለሁ ነው ያሉት፡፡

ዘገባው፡- የአናዶሉ ነው፡፡

*********************************************************************************

ቀን 08/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply