በናይጄሪያ የታጠቁ ሀይሎች አስር ሰዎችን አፍነዉ መዉሰዳቸዉ ተነገረ፡፡በናይጄሪያዋ ኒጀር ከተማ የታጠቁ ሃይሎች አስር ሆስፒታል ሰራተኞችን አፍነዉ መዉሰዳቸዉ ተሰምቷል፡፡የሆስፒታል እና የደህን…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/tRDnIeMy24y6Qcxqf2cEsRU00vnQBkjcJWmTAmTC-zKqp2qywcQkfAH1AbBZCNm2UATf63xJv8RjtQLhT2hVcT_d1Gb43rjrMwm5GssWo-naK3sAKWITKDfpNNcJf_JKi3wi6KpX5MUv6xo6Y2kounF-CXta3dvCQanljMzqkVBebph38JPS7j1MdNDY0OCF4o7WuJjGM8Ic6YWpAspbyhSf6LTyqXMiy5rp9_Oj2qIPq7BVg2m5fWhtR22B1eEAtPIjBvGEJBqwc70lgToTc31_peXk4glV0xtPJb2cHwiC0uyBle08OB7mCwajvMcWJafAhSQD6PNBLmcW6Tr8_Q.jpg

በናይጄሪያ የታጠቁ ሀይሎች አስር ሰዎችን አፍነዉ መዉሰዳቸዉ ተነገረ፡፡
በናይጄሪያዋ ኒጀር ከተማ የታጠቁ ሃይሎች አስር ሆስፒታል ሰራተኞችን አፍነዉ መዉሰዳቸዉ ተሰምቷል፡፡

የሆስፒታል እና የደህንነት ባለሙያዎች አጋቾቹ አስር የሆስፒታል ሰራተኞችን አፍነዉ ከመዉሰዳቸዉ በተጨማሪ፣ ቁጥራቸዉ በግልጽ ያልታወቁ ሰዎችንም መግደላቸዉን ተናግረዋል፡፡

የኒጀር ከተማ ባለስልጣናት እንደገለጹት ኢስላማዊዉ ቡድን ቦኮ ሀራም በከተማዋ ያሉ ብዙ ቁጥር ያላቸዉን ሰዎች አፍኖ መዉሰዱን እና የከተማዋን ነዋሪዎች መንግስትን እንዲቃወሙ በገንዘብ ጭምር እየደለሉ መሆናቸዉን ደርሰንበታል ብለዋል፡፡
የሆስፒታል ምንጮች ከ20 በላይ ሰራተኞቻቸዉ እና አስታማሚ ቤተሰቦች ጭምር ታፍነዉ መወሰዳቸዉን አሳዉቀዋል፡፡

የናይጄሪያ ዶክተሮች ማህበር ፕሬዝዳንት ለሮይተርስ እንደገለጹት በዚህ ዓመት ብቻ 20 የማህበራቸዉ ዓባላት የሆኑ ዶክተሮች ታፍነዉ መወሰዳቸዉን እና አብዛኞቹም በደህንነት ስጋት ምክንያት ሀገራቸዉን ለቀዉ እንዲወጡ መገደዳቸዉን መናገራቸዉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ጥቅምት 09 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply