“በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀመው የማይካድራ ጭፍጨፋ የትህነግ የአማራ ጠልነት ጭንብል የተገለፀበት ክስተት ነው” ረዳት ፕሮፊሰር ጌታ አስራደ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 2 ቀን 2…

“በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀመው የማይካድራ ጭፍጨፋ የትህነግ የአማራ ጠልነት ጭንብል የተገለፀበት ክስተት ነው” ረዳት ፕሮፊሰር ጌታ አስራደ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም… አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው የህውሃት ቡድን በንፁሃን ዜጎች ላይ የፈፀመውን የዘር ጭፍጨፋ የአንደኛ ዓመት መታሰቢያ በጎንደር ከተማ ታስቧል፡፡ የመታሰቢያ ፕሮግራሙን በንግግር የከፈቱት የጎንደር ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ፀጋው አዘዘው እንደገለፁት አሸባሪው የህውሃት ቡድን ከመፈጠሩ ጀምሮ አማራን ለማጥፋት ያልቆፈረው ጉድጓድ ያልፈነቀለው ድጋይ የለም፡፡ የቡድኑ የክሃዲነትና የአረመኔነት ተግባር በማይካድራ በጋይንት በጭና በሰሜን ወሎ እንዲሁም በአፋር ክልል አሳይቶናል፡፡ በዚህ አሸባሪ ቡድን የተደቀነብንን የህልውና አደጋ ለመከላከል አመራሩ የተቆጣ ህዝብ ማንቀሳቀስ ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ውበቱ ደግሞ የአማራ ህዝብ በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ግፍና መከራአሳርፎበታል፡፡አሁንም እያሳረፈበት ይገኛል፡፡ የአማራ ህዝብ በአሸባሪው ቡድን ግፍና መከራ የደረሰበትና እየደረሰበት ያለ ቢሆንም በፈተና ውስጥ በሳት እየተፈነ አለማዝ እየጠነከረ የሄደ ህዝብ ሆኗል፡፡ እየወደቀ እየተነሳ እየተገደለ የአሸባሪውን ቡድን ከቤተ መንግስት ወደ መቀሌ እንዲሸኝ መታገሉን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡ ህውሃት አማራን ሲገድል ሲያፈናቅል ሲያስርና ሲያገላታ ቆይቷል፡፡ይህ አልበቃ ያለው ቡድኑ የማይካድራን የንፁሃን የዘር ጭፍጨፋ ፈፅሟል፡፡ የቡድኑ አረመኔያዊ ድርጊት በማይካድራ የዘር ጭፍጨፋ በግልፅ መስተዋሉን የገለፁት አቶ ዳንኤል ከማይካድራ ዘር ጭፍጨፋ ትምህርት በመውሰድ ቆፍጣና ትውለድ ለመፍጠር መስራት ይገባናል ብለዋል፡፡ በመታሰቢያው ዕለት ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት የጎንደር ዩኒበርስቲ መምህርና የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ጥናት ቡድን መሪ ረዳት ፕሮፊሰር ጌታ አስራደ ደግሞ በጥናት ቡድኑ በተረጋገጠው መሰራት በማይካድራ በሽብር ቡድኑ 1ሽ 563 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 81 ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተረጋጧል፡፡ የዘር ጭፍጨፋው በቡድኑ አደረጃጀት ታግዞ የተፈፀመ ሲሆን ሳምሪ የተባለው የአሸባሪ ቡድኔ ክንፍ የጭካኔ ተግበር እንዲፈፅም ስልጠና ተሰጥቶት የዘር ጭፍጨፋውን መፈፀሙን ረዳት ፕሮፊሰሩ ገልፀዋል፡፡ የማይካድራ ጭፍጨፋ የቡድኑን የአማራ ጠልነት ጭንብል የገለፀ መሆኔን የገለፁት ረዳት ፕሮፊሰሩ የአማራ ህዝብ ታሪካዊ ጠላቴ ነው ብሎ የፈረጀው የአሸባሪው የትህነግ ቡድን እየፈፀመ ያለውን የግፍ ወረራ መመከት ካልቻለ ህልውናው አዳጋ ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በሰማዕታቱ መታሰቢያ ዕለት በተካሄደው ውይይት ከተሳተፉት መካከል አቶ ምስጋናው ጀንበር እንደገለፀት በዩኒበርስቲው የተካሄደው ጥናት ከማይካድራ ባሻገር በሌሎችም የሽበር ቡድኑ ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች የፈፀማቸው ግፎች በሳይንሳዊ ጥናቶችን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ሌላው የውይይቱ ተሳታፊ አቶ ሰለሽ መስፍን ደግሞ የአሸባሪው ቡድን ከእኛ ስብዕና በተቃራኒ በአፍራሽ ተልዕኮ የተገነባ ነው፡፡ የመጣብንን አደጋ ለመመከት የስነ-ልቢና ዝግጅት ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉ አስተያታቸውን ሰጥተዋል፡፡ በዕለቱ የሰማዕታቱ የግፍጭፍጨፋ የህሊና ፀሎት የተደረገ ሲሆን የጧፍ ማብራት ስነ-ስርዓት ተፈፅሟል ያለው የጎንደር ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply