በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ በግንባታ ላይ ያለው የአትክልት መገበያያ ስፍራ በተሻለ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቢሮው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ የአትክልት መገበያያ ስፍራ በመጀመሪያው ምዕራፍ የግንባታ ሂደት እየተገነቡ ካሉ አብዛኛው የመገበያያ ሱቆች በመጠናቀቅ ላይ ናቸው ተብሏል፡፡በአትክልት መገበያያ ስፍራው የመንገድ፣ የመብራት፣ የመፀዳጃ ቤት እና ሌሎች አስፈላጊ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ጎን ለጎን በመካሄድ ላይ እንደሚገኙም ተጠቁሟል፡፡ከ120 በላይ መኪኖዎችን በአንድ ጊዜ ማስቆም የሚችል 3 ሺህ 600 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው የፓርኪንግ እና የ300 ሜትር በ40 ሜትር ስፋት ያለው ዋና መንገድ ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝም የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ሜኤሳ ገልፀዋል፡፡የአትክልት የገበያ ማዕከሉ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን አማካኝነት በ80ሺህ ካሬ ሜትር ላይ በ1 ቢሊዮን ብር ውጪ እየተገነባ ይገኛል፡፡ በመጀመሪያ ምዕራፍ የሚገነቡት ሱቆች እያንዳንዱ 70 ሜትር በ6 ነጥብ 6 ሜትር ስፋት እንደሚኖሩትም ተገልጿል፡፡

*******************************************************************************

ቀን 12/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply