በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ 6 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ…

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ 6 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ትላንት ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ገደማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ልዩ ስሙ “ጀሞ ሚካኤል አደባባይ” አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ በሱቆች ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ቡድን ኃላፊ አቶ ጉልላት ጌታነህ በተለይ ለኢቲቪ ገልጸዋል። በ14 ሱቆች ላይ የእሳት አደጋው ደርሶ በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ኃላፊው ተናግረዋል። የአደጋው መንስኤ እስካሁን እየተጣራ እንደሚገኝ ኃላፊው የገለጹ ሲሆን፣ የእሳት አደጋውን በቁጥጥር ስር ለማዋል 97 የሚሆኑ የእሳት አደጋ ሰራተኞች እና 16 ተሽከርካሪዎች በአደጋው ላይ መሰማራታቸውንም ተናግረዋል። በእሳት አደጋው ወደ 6 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት ጉዳት እንደደረሰበት እና የእሳት አደጋ ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ ወደ 20 ሚሊዮን የሚጠጋ ንብረት ማትረፍ ተችሏል ብለዋል አቶ ጉልላት። እሳቱን ለማጥፋት 3ሺህ 500 ሊትር ውሃ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን፣ እሳቱ ሁለት ሰዓታት የቆየ መሆኑንም ተናግረዋል። ፌዴራል ፖሊስ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የአካባቢው ማህበረሰብ በመተባበር አደጋው በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አቶ ጉልላት ተናግረዋል። ህብረተሰቡ የእለት እለት ተግባራትን በሚያከናውንበት ጊዜ የኃይል አማራጮችን ለእሳት አደጋ በማያጋልጥበት ሁኔታ እንዲጠቀም አቶ ጉልላት ጥሪ አቅርበዋል ያለው ኢትዮ መረጃ ኒውስ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply