በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የታሰሩ 100 የሚደርሱ ባጃጆችን ለመልቀቅ እስከ 8 ሺ ብር ክፍያ ተጠየቀባቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 14 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ሀይሌ ጋርመንት አከባቢ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የባጃጅ ማህበሮች ላይ የአማራ ተወላጆች ይበዛሉ በሚል ከስምሪት ለማስወጣት ከየካቲት 28/2015 ዓ/ም ጀምሮ 100 የሚደርሱ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ ባጃጆች በክፍለ ከተማው መታሰራቸው መዘገቡ ይታወሳል። ፖሊስ እነዚህን ባጃጆች ለመልቀቅ ለእያንዳንዳቸው እስከ 8 ሺህ ብር ክፍያ እየጠየቀ መሆኑን ነው አሽከርካሪዎቹ ለአማራ ድምፅ የገለፁት። በክፍለ ከተማው ለታሰሩ ባጃጆች 4 ሺ ብር እንዲሁም በክሬን ተጭነው ቦሌ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው ለታሰሩ ባጃጆች ደግሞ 8 ሺ ብር በመክፈል አሽከርካሪዎች ንብረቶቻቸውን እንዲወስዱ መመሪያ ውጥቷል ነው የተባለው። በተጨማሪም አሽከርካሪዎቹ በክፍለ ከተማው የተጠየቀባቸውን ክፍያ ከፈፀሙ ቦኋላ ተጨማሪ ለፓርኪንግ 2 ሺ ብር እንዲከፍሉ መገደዳቸውም ተገልጿል። ዘገባው የአማራ ድምፅ ሚድያ ነው።
Source: Link to the Post