በኖርዌይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሙያተኞች ድርጅት ለዩኒቨርሲቲዎች 91 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

በኖርዌይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሙያተኞች ድርጅት ለዩኒቨርሲቲዎች 91 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኖርዌይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሙያተኞች ድርጅት ለአምስት የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች አቅም ግንባታ የሚውል 91 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን ያደረገው “ኢትዮጵያን ኖርዌጃን ፕሮፌሽናል ኦርጋናይዜሽን” የተሰኘ ድርጅት ነው ተብሏል።

የድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተርና በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሳውዝ ኖርዌይ የኮምፒውተር ሳይንስ መምህር የሆኑት ተባባሪ ፕሮፌሰር ሸጋው አናጋው ድርጅቱ የኖርዌይ የልማት ተራድኦ ድርጅት ያዘጋጀውን ውድድር በማሸነፍ ያገኘውን ገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ነው የተናገሩት።

የኖርዌይ የተራድኦ ድርጅቱ በመላው ዓለም ለሚገኙ ታዳጊ ሃገራት የ1 ነጥብ 1 ቢሊየን የኖርዌይ ገንዘብ (ክሮነር) የሚያሸልም ውድድር አውጥቶ እንደነበር አስታውሰዋል።

በውድድሩ ከተካፈሉት 199 ሃገራት መካከል 60 የሚሆኑት ሽልማት ማግኘታቸውን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያን ወክሎ በወድድሩ የተካፈለው ‘በኖሮዌይ የኢትዮጵያ ሙያተኞች ድርጅት’ ከተሸላሚዎች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።

ድርጅቱ በውድድሩ 20 ሚሊየን ክሮነር ወይም 91 ሚሊየን ብር መሸለሙን ነው የገለጹት።

በሽልማቱ ያገኘውን ገንዘብ ለጎንደር፣ ጅማ፣ ሀዋሳ፣ ደብረማርቆስና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የአቅም ግንባታ ስራ እንዲውል ድጋፍ ማድረጉንም ገልጸዋል።

ድጋፉም በስድስት ዓመት ፕሮግራም ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ልዩ ፍላጎት፣ ሜዲካል ቴክኖሎጂ (ኢ ሄልዝ) እና ከኮምፒውተር ጋር የተገኛኙ የትምህርት ክፍሎች በድጋፉ ትኩረት የተሰጣቸው ዘርፎች ናቸው።

በተጨማሪ ድርጅቱ 45 ለሚሆኑ የማስተርስ ተማሪዎች እና 15 የዶክትሬት ተማሪዎች በኖርዌይ የትምህርት እድል እንዲያገኙ የማመቻቸት ስራ እንደሚሰራ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በኖርዌይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሙያተኞች ድርጅት ለዩኒቨርሲቲዎች 91 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply