በአሁኑ ሰአት የህወሓት አመራር ያለበት ቦታ በጥልቀት ይታወቃል ተባለ፡፡                   አሻራ ሚዲያ           ህዳር፡-17/0…

በአሁኑ ሰአት የህወሓት አመራር ያለበት ቦታ በጥልቀት ይታወቃል ተባለ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-17/0…

በአሁኑ ሰአት የህወሓት አመራር ያለበት ቦታ በጥልቀት ይታወቃል ተባለ፡፡ አሻራ ሚዲያ ህዳር፡-17/03/13/ዓ.ም ባህር ዳር በአሁኑ ሰአት የህወሓት አመራር ያለበት ቦታ በጥልቀት የሚታወቅ ቢሆንም መንግስት ለሰላማዊ ዜጎች ደህንነት ትኩረት በመስጠት እርምጃዎችን በተጠና ሁኔታ ነው የምወስደው ብሏል። የህወሓት አመራር በአንድ ላይ እንደማይገኝና በከተማይቱ የተለያዩ ስፍራዎች ተሸሽጎ በወታደራዊ ሬዲዮ እንደሚገናኝ መረጃዎች ያመለክታሉ። የህወሓት ዋነኛ የእዝ ቦታዎች እና ዋሻዎች መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ውስጥ ለውሃ ጉድጓድ በሚል በቻይኖች የተቆፈረ እና በኮንክሪት የተሰራ ሁሉም ነገር የተሟላለት ቪላ ቤት፣ አፄ ዮሀንስ ሙዚዬም ውስጥ የሚገኝ ግራውንድ ቤት፣ ኩያ አካባቢ የሚገኝ ኖብል ሆቴል ህንፃ ስር የሚገኝ ቤት፣ ሀውልቲ አካባቢ የሚገኘው የድምፀ ወያኔ ስቲዲዮ ውስጥ አዳራሽ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪ አፅቢ አካባቢ ባለ ጫካ ውስጥ ለመደበቅ ማታ ማታ መንገድ የመጥረግ ስራ እየሰሩ መሆኑንና በአብረሃ ወፅበሃ ገዳም መሸሸጋቸውንም ተጠቁሟል፡፡ ይህ ቦታ በኮማንዶ የሚጠበቅ ሲሆን የመሳሪያ ክምችት አለበት ተብሎ የሚጠረጠር መሆኑም ተጠቅሷል። ሆኖም የቡድኑ አጠቃላይ ሁኔታ በዚህ ደረጃ ቢታወቅም መንግስት ለሰለማዊ ዜጎች ሲል የተጠና እርምጃ እንደሚወስድ ነው የገለፀው። ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply