በአሁን ሰዓት 15 የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞች በእስር ላይ እንደሚገኙ የኢትዮያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል አስታወቀ፡፡በሀገሪቱ ባለፉት ተከታታይ ሶስት ዓመታት ከፍተኛ የጋዜጠኞች…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/qUOwvjnUTg1dTGumfy_9KZNQSOKInjE_zLndM6AF9bj4erra1gWDM63xwVEUpZui7j2-PoV5Sm5hwCXLmd4ViI7XNPj4lgnpeQvBU22vy3IppSo3e6FBxri-jc-cN_-uPb6xxvX0os0muVfHTbAy9OflLMiGhJAI2VRCfFhwA8C0_hNewLiaSHfLJO1vZ139ZUgXzNh5yc3rWXiPcesfyWOY-GX5bx0bI-em5lFrFjrarubGXDe-BDY-UHVOE-y6XTP81VgHRxRUGS0rcbg3zlM5KmjFfQQHwnLthIVJTUK4DlTbnBMV2_E4KM5URm8Vv8Lq-sfjcFm1h-8bvGLn0Q.jpg

በአሁን ሰዓት 15 የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞች በእስር ላይ እንደሚገኙ የኢትዮያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል አስታወቀ፡፡

በሀገሪቱ ባለፉት ተከታታይ ሶስት ዓመታት ከፍተኛ የጋዜጠኞችና የመብት ተሞጋቾች መታሰራቸውንም ማዕከሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

በያዝነው ፈረጆቹ ዓመት ማለትም በ2023 ዓ.ም ብቻ 47 የሚሆኑ የመብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገው እንደነበር የሚገለፁት የማዕከሉ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ያሬድ ኃይለማርያም ናቸው፡፡

እንደሳቸው ገለፃ ከሆነ ከነዚህ ውስጥ በርካቶች የተፈቱ ቢሆንም አሁንም 15 የሚሆኑ የመብት ተሟጋቾችና ጋዜጠኞች በእስር ላይ እንደሚገኙ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

በየዓመቱ ያለምንም የእስር ትዕዛዝና ያለበቂ ማስረጃ የሚታሰሩ ጋዜጠኞች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱ አሳሳቢ እንደሆነባቸው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ይህንንም በተመለከተ ከመንግስት አካላት ጋር በተደጋጋሚ በመገናኘት ጋዜጠኞቹና ተሟጋቾቹ እንዲፈቱ ጥሪያቸውን ሲያቀርቡ መቆየታቸውንም ነው የገለፁት፡፡

በአሁን ወቅት በእስር ላይ የሚገኙት በርካቶቹ ክስ የተመሰረተባቸው ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆኑ የቀሩት ከአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ክስም ያልተመሰረተባቸው እንዲሁም የታሰሩበትም ቦታ በትክክል እንደማይታወቀ ነው የተናገሩት፡፡

ከነዚህ ውስጥ በተለያዩ የመንግስትና የግል ሚዲያዎች ሲሰራ የቆየው ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው እንደሚገኘበትም ዳይሬክተሩ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ
ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply