በአለማችን በጣት የሚቆጠሩ የናጠጡ ባለጸጎች በ2021 ብቻ ተጨማሪ 421 ቢሊዮን ዶላር ሐብት ማግኘት መቻላቸው ተነገረ፡፡ለመሆኑ እነዚህ ቱጃሮች እነማን አንደሆኑ እና በአመቱ ምን ያክል ገቢ…

በአለማችን በጣት የሚቆጠሩ የናጠጡ ባለጸጎች በ2021 ብቻ ተጨማሪ 421 ቢሊዮን ዶላር ሐብት ማግኘት መቻላቸው ተነገረ፡፡

ለመሆኑ እነዚህ ቱጃሮች እነማን አንደሆኑ እና በአመቱ ምን ያክል ገቢ ማካበት እንደቻሉ ያውቃሉ ?

1ኛ/ ኢለን ማስክ፤ ይህ የምድራችን እጅግ ሐብታም ሰው፤ በዚሁ የፈረንጆቹ 2021 አመት ብቻ ከነበረው የተጣራ ሃብት ተጨማሪ $121 billion ገንዘብ ማግኘት ችሏል፡፡

አሁን ያለው የሀብት መጠኑ ደግሞ $300 billion መድረሱ ተገልጿል፡፡

2ተኛ/ በርናርድ አርናዩልት፤ ይሕ ባለጸጋ በዚሁ አመት ብቻ ተጨማሪ 61 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ ያገኘ ሲሆን በፊት ከነበረው ጋር በድምሩ 176 ቢሊዮን ዶላር የሀብት ክምችት እንዳለው ተገልጿል፡፡

3ተኛ/ ላሪ ፔጅ፤ በዚሁ የአንድ አመት ጊዜ ብቻ ተጨማሪ 47 ቢሊዮን ዶላር ሃብት ማጋበስ የቻለ ሲሆን፤ በፊት ከነበረው ሐብት ጋር ሲደመር ደግሞ 130 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ መሰብሰብ ችሏል፡፡

4ተኛ/ ማርክ ዙከርበርግ፤ ይሕ ቢሊየነር ደግሞ በዚሁ አመት ብቻ በፊት ከነበረው ላይ ተጨማሪ 24 ቢሊዮን ዶላር ሀብትን ያተረፈ ሲሆን፤ አጠቃላይ የሐብት መጠኑ ደግሞ ወደ 128 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማድረግ ችሏል፡፡

5ተኛ/ ቢል ጌትስ፤ ይህ ቢሊየነር ደግሞ በአመቱ 7 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን አጠቃላይ የሐብት መጠኑን ወደ 139 ቢሊየን ዶላር ማሳደግ ችሏል፡፡

6ተኛ/ ጄፍ ቤዞስ፤ በአመቱ 5 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ ያገኘ ሲሆን በድምሩ 195 ቢሊዮን ዶላር የሀብት ክምችት እንዳለው ተነግሯል፡፡

ምንጭ Bloomberg Billionaires Index

ጅብሪል መሀመድ
ታህሳስ 22 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply