በአለማችን 2መቶ 44 ሚሊዮን ህጻናት መማር እያለባቸዉ ከትምህርት ቤት ዉጪ ናቸዉ ተባለ፡፡የክርምቱን ማብቃት ተከትሎ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸዉ እየተመለሱ ቢሆንም በአለም አቀፍ ደረ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/lWLSuTi4yvrdDPdTS0QI66uDNADBqOv1QkxV6U_4FQbxAiOwJ3HiJsmc-R9sparhK8VvULLSBsUaxvBiEOtF-6bI8ArjUO_YhMu64xLaV1vv42wnjptVOt-ovLrQuCDbHSejl7Mt8mynOaJeiG9ldNZyT5jNfnghHmw-GTm951WacMhrVAUezXHkRxDRB2F-icT-kIiQUMHiZgdMaDsdIACxqFocaA-6ZaUxBwfJBTiEIpsbRQaH0xalqMTbrcinpH7uzdtwkAViPEPKpKLIGaEhV1qijEN5-XmrI5-Fp_8nncYYMumXOuReKYcoiymHsUCVKum6NS_t0nBB3hQbZQ.jpg

በአለማችን 2መቶ 44 ሚሊዮን ህጻናት መማር እያለባቸዉ ከትምህርት ቤት ዉጪ ናቸዉ ተባለ፡፡

የክርምቱን ማብቃት ተከትሎ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸዉ እየተመለሱ ቢሆንም በአለም አቀፍ ደረጃ እድሚያቸዉ ከ6 እስከ 18 ዓመት የሆኑ 2 መቶ 44 ሚሊዮን ህጻናት ትምህረት እያገኙ አይደለም ተብሏል፡፡

እንደ አለም ባንክ መረጃ ትምህርት ለኢኮኖሚና ለማህበራዊ ልማት ቁልፍ ሚና ቢጫወትም አሁንም የመማር እድሉ ያላገኙ ልጆች ቁጥር ከፍተኛ ነዉ፡፡
የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በአለማችን ከሚገኙ ልጆች በአማካኝ 12.8 የሚሆነዉን እድሚያቸዉን በትምህረት ያሳልፋሉ ይላል፡፡

በአለማችን ከፍተኛ የሆነ ዕድሚያቸዉን በትምህረት ከሚያሳልፉ መካከል የአዉስትራሊያ ህዝቦች ቀዳሚ ናቸዉ፡፡
የአዉስትራሊያ ዜጎች 21.1 እድሚያቸዉን በትምህርት ሲያሳልፉ የኒዉዝላንድ ህዝቦች ደግሞ 20.3 የሚሆነዉን እድሚያቸዉን ለትምህረት ያዉላሉ፡፡

በአለማችን 5.5 የሚሆነዉን እድሚያቸዉን ለትምህረት በማዋል ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት የደቡብ ሱዳን ዜጎች ናቸዉ፡፡

ማሊና ኒጀር ደግሞ ደቡብ ሱዳንን ተከትለዉ ተቀምጠዋል፡፡
በ2020 አለማችን 5 ትሪሊዮን ዶላር ለትምህርት አዉላለች፡፡
ይህም 4.33 በመቶ የሚሆነዉን የአለማችንን ጂዲፒ ይሸፍናል፡፡

በአባቱ መረቀ
ጳጉሜ 03 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply