በአለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 80 ሚሊየን አለፈ

በአለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 80 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአለም በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 80 ሚሊየን ማለፉ ተገለፀ፡፡

እስካሁን በአለም 80 ሚሊየን 218 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ ከ1 ሚሊየን 757 ሺህ 800 በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

አሜሪካ ከ19 ሚሊየን በላይ ሰዎች በቫይረሱ በመያዝ በቀዳሚነት ተቀምጣለች፡፡

ህንድ፣ ብራዚል፣ ሩሲያ፣ እና ፈረንሳይ በአለም ቫይረሱ ከጸናባቸው አገራት በመሆን እስከ አምስተኛ ደረጃ ይዘዋል፡፡

ደቡብ አፍሪካ በአፍሪካ በወረርሽኙ በጽኑ የተጎዳች ሀገር ስትሆን በከፍተኛ ሁኔታ በቫይረሱ የተያዙ እና ለሞት የተዳረጉ ሰዎች ያሉባት በመሆን በቅድሚያ ትጠቀሳለች፡፡

ሞሮኮ፣ ግብጽ፣ ቱኒዚያ እንዲሁም ኢትዮጵያ ከደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ ቫይረሱ የጸናባቸው ሃገራት በመሆን እስከ አምስተኛ ደረጃ ተቀምጠዋል፡፡

በአንጻሩ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ56 ሚሊየን 480 ሺህ በላይ ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውም ተነግሯል፡፡

ምንጭ፡- ዎርልድ ኦ ሜትር

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በአለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 80 ሚሊየን አለፈ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply