በአለም አቀፍ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የሚሰራ ምክር ቤት መቋቋሙን የኢፌዲሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በሀገር ውስጥ በትራንስፖርቱ ዘርፍ ላይ የሚገኙ 69 ማኅበራትን በማደራጀት 9 ስራ አስፈፃሚዎች በመመደብ ኅብረተሰቡ በየጊዜው የሚያነሳቸውን የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ፣ የመሠረተ ልማት ዝርጋታና ሌሎች የሚነሱ ተያያዥ ቅሬታዎችንና ጉዳዮች ላይ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር በመሆን የሚሰራ ማኅበር መቋቋሙ ይታወቃል፡፡

በቅርቡ ደግሞ አለም አቀፍ የትራንስፖርት አገልግሎቱ ላይ የሚሰራ ካውንስል መቋቋሙን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፡፡ካውንስሉ ኢትዮጵያዊያን እና በውጭ አገር የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ባሉበት አገር ሁነው የትራንስፖርት ዘርፉን ለማሳደግ ባላቸው እውቀትና ተሞክሮ በአለም አገራት ያለውን ተሞክሮ በመውሰድ ዘርፉ በምን ዓይነት መንገድ መጓዝ እንዳለበት የሚያግዝ ነው፡፡ ይህንን ያሉት የትራንስፖርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ፀጋዬ ናቸው፡፡

ጥር 07/2013

አሐዱ ሬዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply