በአለም አቀፍ ደረጃ በአደገኛ እፅ አዘዋዋሪነት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ… በአ…

በአለም አቀፍ ደረጃ በአደገኛ እፅ አዘዋዋሪነት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ… በአለም አቀፍ ደረጃ አደገኛ እፅ አዘዋዋሪነት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ገልጧል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር ምክትል ዳይሬክቶሬት አባላት በዛሬው እለት በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ባደረጉት ፍተሻ መነሻቸውን ላቲን አሜሪካ፣ ሳኦፖሎ ከተማ፣ መዳረሻቸውን ደግሞ የተለያዩ ሀገራት ለማድረግ በአውሮፕላን ሲጓዙ የነበሩት ተጠርጣሪዎችን እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር ኦፕሬሽን ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር መንግስትአብ በየነ ገልጸዋል፡፡ የአደገኛ ዕፅ ቁጥጥር ምክትት ዳይሬክቶሬት በሀገር ውስጥ የሚያበቅሉ፣የሚያዘዋውሩና የሚጠቀሙትን በመከታተል በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ እንደሚያቀርቧቸው የገለጹት ምክትል ዳይሬክተሩ በዛሬ እለትም በጥናት ላይ የተመሰረተ ክትትል በማድረግ 13 ናይጄሪያውያንና አንዲት ብራዝላዊትን ጨምሮ በአጠቃላይ 14 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ጠቁመዋል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከ14 ኪ.ግ በላይ የሚመዝን ኮኬይን የተሰኜ አደገኛ ዕፅ ይዘው የተገኙ ሲሆን አደገኛ ዕፁ በላቲን አሜሪካ አካባቢ የሚመረትና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚዘዋወር መሆኑንም ምክትል ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡ በሶስት ወር ውስጥ ብቻ ወደ 24 የወንጀሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 39 ኪ.ግ ኮኬይንና 36 ኪ.ግ የሚመዝን ካናቢስ የተባለ አደገኛ እፅ መያዛቸው ተገልጿል፡፡ የአደገኛ እፅ ዝውውር በሀገር ላይ የሚያደርሰው ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለትካዊው ጉዳቱ ከፍተኛ በመሆኑ ይህንን ህገ ወጥ ተግባር ለመከላከል የጸጥታ አካላት ለሚያደርጉት ጥረት ህብረተሰቡ ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ኮማንደር መንግስትአብ በየነ ጥሪ አቅርበዋል ሲል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ክፍል ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply