በአልሸባብ ጥቃት 17 ሰዎች ተገደሉ፡፡በሶማሊያ በአሸባሪው አልሸባብ ጥቃት 17 ንጹሃን ዜጎች ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል፡፡አሸባሪ ቡድኑ በስሌይ ተብሎ በሚጠራው የሶማሊያ ወታደራዊ ማዘዣ ጣበያ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/X5S0q15TPalK5CXR8G77wVd_uuh_qKum0N_rGM7RxqqPp1pdFNRwPyJCL1njkwll5UIoOjLXeKyYsTJ1kH3A_KsmRp9Rk5fjLO8xBN9u0HXFIznKAGo8auFFHr89Ev65XgIzgaM99IDYN0dWWRKJOqtOScepCrQxlTLIx4qcJvjYOxVXOcByS_c0hiDcjcE_VfXSUIt2hq1Z0SV4x18EdUJ5cXvMkldBKWjlGd7YnBUtDaOBUqExxlNCFeEgK9TJGA8VbGPX1xGqiVKARk-swAo9vi7ADvUD_F84P6RDwVDsqn2g8zDJWPmx1ui4fgOV54-f_mmrSjd05q45xzPnHQ.jpg

በአልሸባብ ጥቃት 17 ሰዎች ተገደሉ፡፡

በሶማሊያ በአሸባሪው አልሸባብ ጥቃት 17 ንጹሃን ዜጎች ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል፡፡

አሸባሪ ቡድኑ በስሌይ ተብሎ በሚጠራው የሶማሊያ ወታደራዊ ማዘዣ ጣበያ ላይ ባደረሰው ጥቃት ንጹሃን ዜጎች መገደላቸው ታውቋል፡፡

ሶማሊያን እያመሳት የሚገኝው አሸባሪ ቡድኑ የሃገሪቱ ደቡብ ምዕራብ አካባቢ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩ ተገልጻል፡፡

አልሸባብ በዚህ አካባቢ ባደረሰው ጥቃት ምክንያት ዜጎች አካባቢውን ጥለው እየወጡ እንደሆነም ተንግሯል፡፡

አንድ የሶማሊያ ከፍተኛ ባለስልጣን እንደተናገሩት ከሆነ አሸባሪ ቡድኑ እያደረሰ ያለው ጥቃት ከፍተኛ መሆኑን ተናግረው አልሸባብ ሲቆጣጠራቸው ከነበሩ ዋና ዋና ከተሞች እና መንደሮች ማፈግፈጉ “የመጨረሻቸው መጀመሪያ ይመስለኛል ብለዋል፡፡

ጥቃቱን ተክትሎም ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንደለው የሚነገርለትና የቀጠናው ስጋት የሆነው ታጣቂ ቡድን አልሻባብ፤ ከዋና ዋና ወታደራዊ ይዞታዎቹ እያፈገፈገ ነው ተብሏል።(አፍሪካ ኒውስ)

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply