በአልጣሽ ብሄራዊ ፓርክ ጉዳይ የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች እና በፓርኩ አዋሳኝ የሚኖሩ የሁሉም ቀበሌ ነዋሪዎች የደን ሃብቱን ከውድመት እንዲከላከሉ ጥሪ ቀረበ፤ በአልጣሽ ብሄራዊ ፓርክ ትናንት…

በአልጣሽ ብሄራዊ ፓርክ ጉዳይ የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች እና በፓርኩ አዋሳኝ የሚኖሩ የሁሉም ቀበሌ ነዋሪዎች የደን ሃብቱን ከውድመት እንዲከላከሉ ጥሪ ቀረበ፤ በአልጣሽ ብሄራዊ ፓርክ ትናንት የነበሩ ደኖችን የማጥፋት ቃጠሎ እየተከሰተ ስለ መሆኑም ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 7 ቀን 2015 ዓ/ም … አዲስ አበባ ሸዋ በአልጣሽ ብሄራዊ ፓርክ ትናንት የነበሩ ደኖችን የማጥፋት ቃጠሎ እየተስተዋለ መሆኑን የገለጸው የቋራ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን በበርሚል ቀበሌ በነበረው ቆይታ የታዘበውን አጋርቷል። በቆይታውም የአልጣሽ ብሄራዊ ፓርክን የተፈጥሮ ሃብት ከአሁኑ የማውደም ስራ ላይ የተጠመዱ አካላት ስለመኖራቸው ጠቁሟል። በአልጣሽ ብሄራዊ ፓርክ የሚመለከታችሁ የስራ ክፍሎች እና በፓርኩ አወሳኝ የምትኖሩ የሁሉም ቀበሌ ነዋሪዎች የደን ሃብቱን ከውድመት እንድትከላከሉ ሲልም ጥሪውን አስተላልፏል። የፓርኩ መኖር በአካባቢው ለምትገኙ ማህበረሰቦች፣ ለወረዳውና ለመላ ሃገራችን በቱሪዝም ሃብቱነቱና በኢኮኖሚ ዘርፍ በርካታ ጥቅሞችን መስጠት የሚችል ፓርክ መሆኑን አውቀን ትኩረት በመስጠት መንከባከብና ከውድመት መጠበቅ ይኖርብናል የሚል መልዕክትም አስተላልፏል። ከፓርኩ እና ከፓርኩ ውጭ የደን ሃብቱ ከአሁኑ ጀምሮ መቃጠል ከተጀመረ በረሃማነት እየተስፋፋ በአካባቢው ምርትና ምርተማነትን በዘላቂነት እንደይረጋገጥ የሚያደርግ በመሆኑ ሁሉም አካል ለተፈጥሮ ሃብቱ ትኩረት መስጠት መቻል ይኖርበታል እያልን የቅድመ ጥንቃቄ ሃሳባችንን እናስተላልፋለን ብሏል የቋራ ወረዳ ኮሚኒኬሽን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply