You are currently viewing በአማራው ትግል ላይ የአብን መስራች፣አባል እና አመራር በመሆን የሚንቀሳቀሰው አሸናፊ አካሉ  መታፈኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ      ጥር 7 ቀን 2015 ዓ/ም ……

በአማራው ትግል ላይ የአብን መስራች፣አባል እና አመራር በመሆን የሚንቀሳቀሰው አሸናፊ አካሉ መታፈኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 7 ቀን 2015 ዓ/ም ……

በአማራው ትግል ላይ የአብን መስራች፣አባል እና አመራር በመሆን የሚንቀሳቀሰው አሸናፊ አካሉ መታፈኑ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 7 ቀን 2015 ዓ/ም … አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) መስራች፣ አባል እና የምዕራብ ጎጃም ዞን አመራር በመሆን ስለሰፊው የአማራ ህዝብ ከፍተኛ ትግል በማድረግ የሚታወቀው አሸናፊ አካሉ ጥር 7/2015 የአፈና እስር ተፈጽሞበታል። በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ከባለእግዚአብሔር ጀርባ ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤቱ ጥር 7/2015 ከቀኑ 10:30 ገደማ በመጡ ቁጥራቸው ከ20 የማያንሱ የአድማ ብተና አባላት ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ ታፍኖ ስለመወሰዱ አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከቤተሰብ ያገኘው መረጃ አመልክቷል። በእለቱም አሸናፊ አካሉን ለማፈን ተልዕኮ ተሰጥተዋል ከተባሉ የጸጥታ አካላት ጋር የቃላት ልውውጥ ሲያደርግ እንደነበር ተገልጧል። አሸናፊ አሁን ላይ በባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ አዲሱ መናኽሪያ መሄጃ አማራ ብረታ ብረት ጎን አመዶ ገበያ አካባቢ ባለ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ እንደሚገኝ ተገልጧል። በቅርብ የተመለከቱ የዐይን እማኞች እንደሚሉት አሸናፊ በጣቢያው ግቢ ከእስረኞች ተለይቶ ውጭ ላይ ለሰዓታት እንዲቀመጥ ተደርጓል። ይሁን እንጅ ከምሽቱ 1:30 አካባቢ ጀምሮ ደግሞ ሞተሩ በጠፋ ፓትሮል ውስጥ በማስገባት አስቀምጠውት ይገኛሉ ተብሏል። በግቢው ውስጥም ሁለት ፓትሮል እንደሚታይም አሚማ ያነጋገራቸው የዐይን እማኞች ገልጸዋል፤ እንደ እነሱ አገላለጽም ምንአልባት አሸናፊን ወደ ሌላ አካባቢ ሊያዘዋውሩት ይችላሉ። አሸናፊ ከከተማው ይልቅ እንዲገባ የተደረገው በዙሪያ ወረዳ ጣቢያ በመሆኑም ለርክክብ የተቸገሩበት ሁኔታ ስለመኖሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ምግብ፣ ውሃ እና አልባሳት ወስደው ለመስጠት የፈለጉ ቤተሰቦችም ወደ ጣቢያው በመሄድ ለማነጋገር ቢሞክሩም አሸናፊ ወደ ሌላ ቦታ ሊወሰድ ይችላል የሚል አጠራጣሪ የሆነ መረጃ በማግኘታቸው አልተሳካላቸውም። አሸናፊ በጣቢያው ፍላጎትና ትዕዛዝ እንዳልታሰረ ከቤተሰብ የተገኘው መረጃ አመልክቷል። አሸናፊ አካሉ ከአሁን ቀደም በግንቦት 2014 ዓ/ም የብልጽግናው አገዛዝ በነቁ የአማራ ልጆች ላይ ባደረገው የዘመቻ እስር ወቅት ታፍነው ወደ ጎንደር ጋይንት ነፋስ መውጫ ተወስደው ከአንድ ወር በላይ ከተሰቃዩት የግፍ እስረኞች መካከል አንዱ መሆኑ ነው። አሸናፊ አካሉ በትሕነግ መራሹ ጸረ አማራው ስርዓት ለበርካታ ዓመታት በተለያዩ እስር ቤቶች አያሌ ግፍ እና በደል የተፈጸመበት የአማራ ታጋይ መሆኑም ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply