You are currently viewing “በአማራ ህዝብ ላይ በሚደርሠው ዘርፈ ብዙ እንግልት እና መሰደድ ፣ሞት እና መፈናቀል እንዲሁም የኢኮኖሚ ስብራት ቀዳሚ ገፈት ቀማሽ የሆነው የወሎ አማራ ህዝብ ከችግሩ ሲያገግም ለተደራራቢ ሰው…

“በአማራ ህዝብ ላይ በሚደርሠው ዘርፈ ብዙ እንግልት እና መሰደድ ፣ሞት እና መፈናቀል እንዲሁም የኢኮኖሚ ስብራት ቀዳሚ ገፈት ቀማሽ የሆነው የወሎ አማራ ህዝብ ከችግሩ ሲያገግም ለተደራራቢ ሰው…

“በአማራ ህዝብ ላይ በሚደርሠው ዘርፈ ብዙ እንግልት እና መሰደድ ፣ሞት እና መፈናቀል እንዲሁም የኢኮኖሚ ስብራት ቀዳሚ ገፈት ቀማሽ የሆነው የወሎ አማራ ህዝብ ከችግሩ ሲያገግም ለተደራራቢ ሰው ሰራሽ ችግር እየተጋለጠ ይገኛል።” ወሎ ቤተ አምሐራ የልማትና በጎ አድራጎት ድርጅት አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሀምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ መነሻቸውን ወሎ አድርገው አዲስ አበባ ለመግባት እንግልት የሚደርስባቸውን ወገኖች አስመልክቶ ከወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና በጎ አድራጎት ድርጅት የተሠጠ መግለጫ:_ በአማራ ህዝብ ላይ በሚደርሠው ዘርፈ ብዙ እንግልት እና መሰደድ ፣ሞት እና መፈናቀል እንዲሁም የኢኮኖሚ ስብራት ቀዳሚ ገፈት ቀማሽ የሆነው የወሎ አማራ ህዝብ ከችግሩ ሲያገግም ለተደራራቢ ሰው ሰራሽ ችግር እየተጋለጠ ይገኛል። የመልካም ዕሴት ባለቤት የሆነውና የኢትዮጵያዊነት ተምሳሌት ተደርጎ የሚወሠደው ህዝባችን ከዚች ሀገር ቅደመ ምስረታ እስከሁን ድረስ ሀገራዊ ዕሴትን ለማጎልበት እንደ ዜጋ የራሱን ትልቅ አበርክቶ የተወጣ ነው ብለን እናምናለን። ለዚህም ማሳያ ስሙ ለሌሎች ተምሳሌት እስከመሆን እና ለሀገራችን ቱሪዝም ከፍተኛ የገቢ ምንጭ እስከመሆን የደረሡ የቱባ ባህል በርካታ የቱሪዝም መዳረሻ ባለቤት የሆነው የወሎ አማራ ህዝብ በጦርነት የዳሸቀው ኢኮኖሚው ከጦርነት ማግስትም በዘረፈ ብዙ ምክንያቶች እየተጎዳ ይገኛል፡፡ በተለይ በሰሜን ወሎ እና በዋግኽምራ በጦርነት የደረሠው ጠባሳ እስከ አሁን ባለመሻሩ ንፁሀኖች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው መሰረተ ልማቶች በመውደማቸው የኤሌክትሪክ የመብራት፤ የውሃ፤ የወፍጮ፤ የጤና የትምህርት አገልግሎት ሳይኖር በጨለማ መከራውን እንዲያይ እስካሁን ድረስ ተፈርዶበታል፡፡ ከእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማንለው መልኩ ከሦስት አስር አመታት ወዲህ በህዝባችን ላይ የደረሠው ማቆሚያ ያጣ በደል እጅግ አሳዛኝ እና ማቅ የሚያስለብስ ነው። ህዝባችን ይህን ሁሉ ታግሶ አሁንም ሀገራዊ ስሜት እንዳይላላ እየከፈለ ያለው መስዋትነት ተዘንግቶ ከሌሎች ሀዝቦች ጋር ባቀናው ከተማ ባዳ ነሀ አትገባም መባሉ እጅጉን አሳስቦናል። ወደ አዲስ አበባ ከተማ በአራቱም ማዕዘን በየቀኑ ለተለያዩ ጉዳዩች ማለትም ለትምህርት ፣ለንግድ፣ ለህክምና ለተለያዩ ጉዳዮች ዜጎች መብታቸውን ተጠቅመው ቢንቀሳቀሱም በዚህ የክረምት ወራት ከአማራ ክልል መነሻቸውን ወሎ ያደረጉ ተጓዦች ግን ኦሮሚያ ክልል ሲደርሡ የክፍለ ሀገር መታወቂያ ያለው ሰው ወደ አዲስ አበባ አትገቡም ተብለው ለከፍተኛ እንግልት ኪሳራ እየደረሰባቸው ነው። ይህ ከተሠማ ሳምንታት የተቆጠረ ቢሆንም ድርጅታችን ወሎ ቤተ አምሐራ የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅትም ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ የነበር ሲሆን በቅርብ ቀናት መፍትሄ ይሰጣል በማለት በዝምታ የቆየ ሲሆን እስከ አሁን ችግሩ ባለመፈታቱ የወገኖቻችንን መንገላታት ይቆም ዘንድ አጥብቆ በሰላማዊ መንገድ የሚመለከተውን አካል ይጠይቃል፡፡ የመንግስት ስጋት ከፀጥታ ጋር የተያያዘ ከሆነ መንግስት የሚጠበቅበትን የደህንነት ስራ በመስራት የብዙሀኑን የዜጎችን በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት ማክበር እና ማስከበር ይገባዋል እንጂ በጅምላ በጭፍን ፍርድ ሁሉንም ሰው እንቅስቃሴውን መገደብ ተገቢ አይደለም። የዞኑም ሆነ የኦሮሚያ ክልል እና የፌደራል መንግስት ይሄንን የዜጎችን በማንኛውም ቦታ የመንቀሳቀስ መብት እንዲያከብር እና እንዲያስከብር ከግዙፍ ስህተቱም በመማር አስቸኳይ መፍትሔዎችን እንዲሰጥ በዚህ አስነዋሪ ተግባር የተሳተፉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እና በህዝባችን ላይ ለደረሠው እንግልት ይቅርታ ጠይቆ ድጋሜ ይህ አይነት ተግባር እንዳይፈፀም ስንል ማሣሠብ እንፈልጋለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply