“በአማራ ህዝብ ላይ በሚፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል አዝነን እና ተቆጥተን ብቻ የህዝባችንን ዕልቂት በዝምታ የማንመለከት መሆናችንን ወዳጅም ጠላትም ሊያውቀው ይገባል።” ሲል የአማራ ዴሞክራሲ…

“በአማራ ህዝብ ላይ በሚፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል አዝነን እና ተቆጥተን ብቻ የህዝባችንን ዕልቂት በዝምታ የማንመለከት መሆናችንን ወዳጅም ጠላትም ሊያውቀው ይገባል።” ሲል የአማራ ዴሞክራሲ…

“በአማራ ህዝብ ላይ በሚፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል አዝነን እና ተቆጥተን ብቻ የህዝባችንን ዕልቂት በዝምታ የማንመለከት መሆናችንን ወዳጅም ጠላትም ሊያውቀው ይገባል።” ሲል የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ አዴኃን ስራ አስፈጻሚ ገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ አዴሃን ስራ አስፈጻሚ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ድርጅቱ ተስፋ አድርጓቸው የነበሩ እና የለውጡ ኃይል ይተገብራቸዋል ብሎ በዛሬ ነገ ሲጠባበቃቸው የነበሩ ጉዳዮች ሁሉ የውሃ ሽታ በመሆናቸው ብቸኛ ተስፋው የሆነውን የአማራን ህዝብ በተደራጀ መልኩ ሁለንተናዊ ትግል እንዲያደርግ ጥሪ ያቀርባል ነው ያለው። በአማራ ላይ የሚፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲቆም ማንኛውንም መስዋትነት እንከፍላለን ያለው አዴኃን እንደ አማራ ብሎም እንደ ኢትዮጵያ ሐቀኛና መዋቅሩን የዘረጋ ድርጅት መሆኑን ጠቅሷል። በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ጋንሎ ቀበሌ የተፈጠመውን የዘር ፍጅት በዝምታ ማለፍ ህሊናችን የማይቀበለው በመሆኑ የሕዝባችንን ህልውና ለማስጠበቅ እኛም ቀድመን መስዋትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናችን ለመግለፅ እንወዳለን ብሏል። የጥቃቱ ሰለባ የሆነው የአማራ ህዝብም ተፈጥሯዊ መብቱን ለመጠቀም በያለበት እንዲደራጅ እንጠይቃለን ሲል አሳስቧል። በአማራ ላይ ግልፅ የሆነ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተከናወነ ባለበት ሁኔታ መንግስት ማስቆም ባለመቻሉ ዋና ተጠያቂ ነው ብሏል። የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ነፍጥ አንስቶ ዋና መቀመጫውን ኤርትራ በረሃ አድርጎ በዱር በገደሉ ለአማራ ህዝብ ሲታገል የቆየ ድርጅት ስለመሆኑ ያወሳው አዴኃን ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ በሠላማዊ መንገድ እየተቀሳቀሰ ይገኛል ሲል አስታውቋል። በሠላማዊ መንገድ በህዝባችን ላይ የሚደረሰውን የዘር ማጥፈት ወንጀል ቅድሚያ ትንበያ በመስጠት ጭምር እንዲያስቆም ስንጠይቅ ነበር ያለው ድርጅቱ ዳሩ ግን ማስቆም ቀርቶ በከፍተኛ መጠን ቁጥሩ እየጨመረ አሰቃቂነቱ እየከፋ መጥቷል ብሏል። ይህ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል አይደለም ለአማራ ህዝብ ህልውና መብት እና ጥቅም ለማስጠበቅ ለተቋቋመ ድርጅት ቀርቶ ማንኛውንም ሰዋዊ የሆነ ግለሰብ እና ድርጅት ያሳዝናል፣ ያስቆጣልም ነው ያለው። የተፈፀመው ጭፍጨፋ አሳዝኖናል፣ አስቆጥቶናልም ያለው አዴኃን አዝነን እና ተቆጥተን ብቻ የህዝባችንን ዕልቂት በዝምታ የማንመለከት መሆናችንን ወዳጅም ጠላትም ሊያውቀው ይገባል ብሏል በመግለጫው። መንግስት ብሄራዊ የሀዘን ቀን እንዲያውጅ የጠየቀው የአዴኃን ስራ አስፈጻሚ በመጨረሻም የአማራ ብልፅግና በአስቸኳይ በአማራ ስም የተደራጅ የፖለቲካ ፖርቲዎችን እና ሲቪክ ድርጅቶችን ስብሰባ እንዲጠራ አጥብቀን እጠይቃለን ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply