በአማራ ህዝብ ላይ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በታጠቁና በተደራጁ አካላት እየተፈፀመ ላለው እልቂት መንግስት ከተጠያቂነት አያመልጥም ሲሉ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) የድ…

በአማራ ህዝብ ላይ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በታጠቁና በተደራጁ አካላት እየተፈፀመ ላለው እልቂት መንግስት ከተጠያቂነት አያመልጥም ሲሉ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) የድ…

በአማራ ህዝብ ላይ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በታጠቁና በተደራጁ አካላት እየተፈፀመ ላለው እልቂት መንግስት ከተጠያቂነት አያመልጥም ሲሉ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ራስ ወርቅ መላኩ ገለፁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ላይ እየተፈፀመ ስላለው ዘርፈ ብዙ ግፍና በደል መንስኤውና መፍትሄው ምንድን ይላሉ ስንል የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ራስ ወርቅ መላኩን አነጋግረናል። አቶ ራስ ወርቅ መላኩ ሲቀጥልም በእርግጥም በአማራ ላይ የሚፈፀመው ግፍ ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን ላለፉት 50 ዓመታት የዘለቀ መሆኑን አውስተዋል። በተከይም ባለፉት 27 ዓመታት በህወሀት መራሹ የኢህአዴግ ስርዓት ጠንሳሽነትና በብአዴን ተቀባይነት ተለይቶ ግድያና መፈናቀል ሲደርስበት እንደነበርና ይህም ለትግል ማነሳሳቱን ተከትሎ ከሀገር ውስጥ እስከ ኤርትራ በርሀ ድረስ በመሄድ አደረጃጀት በመፍጠር ትግል መደረጉን ጠቅሰዋል። የአማራ ህዝብ ለውጥ እንዲመጣ በሚል በአደባባይ፣በጫካ እና በእስር ቤት ሳይቀር ልጆቹን ገብሮ እየነጋ ነው በሚል ተስፋ የሰነቀበት የለውጥ ኃይል ነኝ ያለውም ህዝቡ የታገለለትን መብት፣ጥቅምና ፍላጎት ማስከበር አልቻለም፤ ጥያቄዎቹን እየመለሰ አይደለም ብለዋል። አማራ ዛሬም በመተከል፣በወልቃይት፣ጠገዴ፣ራያ፣ በሸዋ ደራ እና በሌሎችም አካባቢዎች ዘርፈ ብዙ ጥቃት እየተፈፀመበት ቢሆንም የፌደራል መንግስትና የአማራ ክልል መንግስትም ህዝብ እንደ ህዝብ ተለይቶና ተፈርጆ ሲጨፈጨፍ መታደግ አለመቻሉ ከተጠያቂነት አያድነውም ሲሉም አክለዋል። በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በማንነቱ ጥቃት እየተፈፀመበት ላለው አማራ፣ የአማራ ክልል ብልፅግና በተቆርቋሪነት ጠንካራ ስራ እየሰራ ያለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል። በመተከል እየተፈፀመ ላለው እልቂት የህወሀት፣የኦነግ ሸኔ እና የሱዳን ብሎም የግብፅ ኃይሎች እጅ እንደሚኖርበት የጠቀሱት አቶ ራስ ወርቅ የፌደራል መንግስት ልክ ሶማሌ ክልል ላይ እንዳደረገው ጣልቃ ገብነት እጁን አስገብቶ መፍትሄ ማምጣት አለበት ብለዋል። በወልቃይት፣በጠገዴ፣በራያ፣በመተከል፣በሸዋ ደራ እና በሌሎችም አካባቢው እየደረሰ ላለው ችግር መፍትሄ ያገኝ ዘንድ የአማራ ክልል መንግስት ከፌደራል መንግስት ጋር በመነጋገር እልባት እንዲያገኙ ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል። የፌደራል መንግስት በንፁሀን ላይ እልቂት እየፈፀመ ባለው በህወሀት እና በመሰሎቹ ላይ እያሳየ ያለው እሽሩሩ አካሄድን ግን እንዳልወደዱት ነው የተናገሩት። ከአዴኃን የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ከአቶ ራስ ወርቅ መላኩ ጋር የተደረገውን ቆይታ በአማራ ሚዲያ ማዕከል የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply