በአማራ ህዝብ ላይ በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ጭፍጨፋን ለማውገዝና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማጋለጥ ያለመ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራታቸውን በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የአማራ ኮሚኒቲ…

በአማራ ህዝብ ላይ በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ጭፍጨፋን ለማውገዝና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማጋለጥ ያለመ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራታቸውን በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የአማራ ኮሚኒቲ…

በአማራ ህዝብ ላይ በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ጭፍጨፋን ለማውገዝና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማጋለጥ ያለመ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ መጥራታቸውን በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የአማራ ኮሚኒቲ ማህበራትና ሲቪክ ድርጅቶች አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የአማራ ኮሚኒቲ ማህበራትና ሲቪክ ድርጅቶች ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም በአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን የጠራውን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ አስመልክቶ የድጋፍ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል። በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክትም በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን መንግስት መር ስርዓታዊ የዘር ጭፍጨፋን የአለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲገነዘብ እና ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጥ ለማድረግም ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚጠሩ ገልፀው ነበር። በዚህም መሰረት የተለያዩ የሀገር እና የወገን ተቆርቋሪ የሆኑ ስብስቦችን/አደረጃጀቶችን፣ የሚዲያ ተቋማትና ግለሰቦችን በማስተባበር የፊታችን ኖቬምበር 20,2020፣10 AM ላይ በዋሽንግተን ዲሲ እና በሌሎችም የሰሜን አሜሪካ ከተሞች በአንድ ቀን የሚደረግ ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ስለማዘጋጀታቸው ነው ያስታወቁት። በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የአማራ ኮሚኒቲ ማህበራትና ሲቪክ ድርጅቶች እንደገለፁት ሰላማዊ ሰልፉ ኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስት መዋቅር የቀጥታ ተሳትፎና ጠ/ሚ አብይ አህመድ በሚመሩት ድርጅት ኦህዴድ የፋይናንስና ወታደራዊ ድጋፍ በሚደረግላቸው ፅንፈኛ ሀይሎች አማካኝነት በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀልን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማጋለጥ ያለመ ነው። ጠ/ሚ አብይ አህመድ የሚመሩት አስተዳደርም የዜጎችን ደህንነትን የመጠበቅ ቀዳሚ መንግስታዊ ኃላፊነቱን አልተወጣም ያሉት ማህበራቱ በወንጀሉ በቀጥታ በመሳተፍ፣ፅንፈኞችን በፋይናንስና በስልጠና በመደገፍ የዘር ጭፍጨፋው አካል ሆኗል ሲሉ ወቅሰዋል። ከዚህም ባሻገር በአማራ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ተራ ግጭት ለማስመሰልና ወንጀሉን ለመሸፋፈን በታቀደ መንገድ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ልዩ ልዩ የትኩረት ማስቀየሪያ መንገዶችን በመተግበር እንዲሁም የዘር ማጥፋት ወንጀሉን በሰላማዊ መንገድ ለመቃወም የሚወጡ ዜጎችን በማፈን ወንጀሉ እንዳይጋለጥና ጭፍጨፋውም እንዲቀጥል እየሰራ ይገኛል ሲሉ መንግስትን ከሰዋል። የአማራ ህዝብ በማንነቱ ተለይቶ በህይወት የመኖር ተፈጥሮአዊ መብቱን ተከልክሎ በተገኘበት ቦታ ሁሉ ኢሰብአዊ በሆነ መልኩ ሲጨፈጨፍ ድርጊቱን ለመቃወም ሰው መሆን በቂ ስለሆነና ከዛም በላይ ሀገር የሚባለው ፅንሰ ሀሳብ ያለህዝብ ከንቱ መሆኑን በመገንዘብ የአማራ ህዝብ እየደረሰበት ያለውን ስርዓታዊ የዘር ጭፍጨፋን ለመቃወም በጠራነው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በመሳተፍ እንደ ሰው፣ እንደ ህዝብና እንደ ሀገር የሚያስተሳስረንን ውል ለወገናችሁ ድምፅ በመሆን በተግባር እንድታሳዩ ሲሉ በሰሜን አሜሪካ ለሚገኙ አማሮችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ጥሪ አቅርበዋል። በዩኤስ ካፒታል ግራውንድ ዋሽንግተን ዲሲ በሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍም ራስን ብሎም ወገንን ከኮሮና ለመከላከል የሚያስችል የአፍ መሸፈኛ ጭምብል/ማስክ ማድረግን እንዳትረሱ ሲሉ አሳስበዋል። በሌሎች የሰሜን አሜሪካ ከተሞች በተመሳሳይ ቀን የሚደረጉ ሰልፎችን በተመለከተ ዝርዝር መረጃን ወደፊት እንደሚያሳውቁ የገለፁት የተቃውሞ ሰልፉን የጠሩትና በዋናነት የሚያስተባብሩት በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የአማራ ኮሚኒቲ ማህበራትና ሲቪክ ድርጅቶች ናቸው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply