በአማራ ህዝብ ላይ በተደጋጋሚ  የሚፈጸመውን የዘር ጭፍጨፋ ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እንደሚያወግዝ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ግርማው አሸብር ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/…

በአማራ ህዝብ ላይ በተደጋጋሚ የሚፈጸመውን የዘር ጭፍጨፋ ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እንደሚያወግዝ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ግርማው አሸብር ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/…

በአማራ ህዝብ ላይ በተደጋጋሚ የሚፈጸመውን የዘር ጭፍጨፋ ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እንደሚያወግዝ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ግርማው አሸብር ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ማንነትን መሰረት በማድረግ በአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጅምላ ጭፍጨፋን የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እንደሚያወግዝ ተገልጧል። በሰላማዊና በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸም ግድያም የኋላቀሮችና የኢትዮጵያዊነት ስብዕና የሌላቸው ባዕዳን አካላት መገለጫ መሆኑን የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ግርማው አሸብር አውስተዋል። ዜጎች በሰላምና በህይወት የመኖር ተፈጥሯዊ መብታቸውን የማስጠብቅ የመንግስት የመጀመሪያው ሃላፊነት በመሆኑ ለወደፊትም በግልጽ እየጎላ የመጣው የአማራ ህዝብ ላይ ዘርን መሠረት ያደረገ ግድያ በአስቸኳይ እንዲቆም ሲሉ ነው ለመንግስት ጥሪ ያቀረቡት። በንጹሃን የአማራ ወገኖች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግድያና ጭፍጨፋ በብሔራዊ ደህንነት ላይ የተጋረጠ ከፍተኛ አደጋ መሆኑን ያወሱት ዳይሬክተሩ ለአገር አንድነትም ትልቅ እንቅፋት በመሆኑ በቤንሻንጉል መተከል ዞን ፣ በደቡብ ክልል ጉራፈርዳ ፣ ሰሞኑን ደግሞ በኦሮምያ ምዕ/ወለጋ በግልጽ አማራ ላይ ያነጣጠረ የዘር ጭፍጨፋ ተፈፅሟል። ይህም ለአገር አንድነት ከፍተኛ አደጋ ከመሆኑ በተጨማሪ በአማራ ህዝብ ህልውና ላይ በይፋ ከልካይ አልባ ፍጅት እየተፈጸመ በመሆኑ መንግስት አስፈላጊውን ሰላም የማስፈን እና የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ሲሉ አቶ ግርማው ጥሪ አቅርበዋል። የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply