በአማራ ህዝብ ላይ በፀረ አማራ ኃይሎች አማካኝነት በተደጋጋሚ የሚፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ይቁም! አማራ ሚዲያ ማዕከል  ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ በአማ…

በአማራ ህዝብ ላይ በፀረ አማራ ኃይሎች አማካኝነት በተደጋጋሚ የሚፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ይቁም! አማራ ሚዲያ ማዕከል ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማ…

በአማራ ህዝብ ላይ በፀረ አማራ ኃይሎች አማካኝነት በተደጋጋሚ የሚፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ይቁም! አማራ ሚዲያ ማዕከል ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ላይ ከሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 2013 ዓ.ም ብቻ በሽብር ተግባር በተሰማሩ ፀረ አማራ ታጣቂ ቡድኖችና በመንግስት መዋቅሩ ባሉ ተባባሪዎቻቸው እገዛ 6 ጊዜ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል። ከሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 22 ቀን 2013 ዓ.ም በ4 ወራት ውስጥ ብቻ በአማራ ህዝብ ላይ 6 ጊዜ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፅሟል። ይኸውም:_ 1)ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት አካባቢ አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ባልታወቁ አካላት ከተገደለበት ምሽት ጀምሮ ሰኔ 23 እና 24 ቀን 2012 ዓ.ም በተከታታይ ቀናት በኦነግ እና በኦዴፓ ተባባሪዎቹ አማካኝነት በተፈፀመው አማራ እና ኦርቶዶክሳውያን ተኮር ጭፍጨፋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ህይወታቸው አልፏል፤አካላቸው ጎድሏል፤ በቢሊዮን የሚገመት ሀብት ንብረት ወድሟል። 2)ጳጉሜ 1 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽት ጀምሮ በመተከል ዞን በቡለንና ወምበራ ወረዳዎች በተለይም በኤጳር እና በመልካ ቀበሌዎች በጉምዝ ታጣቂዎችና በመንግስት ሚሊሻዎች ግብረአበርነት ያለማንም ከልካይ ከ160 በላይ በሚሆኑ አገው/አማራዎች ላይ የለየለት የጅምላ አሰቃቂ ግድያ የመፈፀሙም ይታወሳል። 3)በተጨማሪም 3 ሳምንታት ባልሞላ ጊዜም በተመሳሳይ በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ልዩ ስሙ በንገዝ በተባለ ቀበሌ መስከረም 14 ለ15 ቀን 2013 ዓ.ም ሌሊት ላይ የታጠቁ ነፍሰ ገዳዮችና ተባባሪዎቻቸው በአካባቢው ነዋሪ በሆኑ ንፁሀን የአማራ ተወላጆች ላይ በፈፀሙት ዘር ተኮር ግድያ ቢያንስ 14 አማራዎች ተገድለዋል። 4) ጥቅምት 8ለ9 በቤንች ሸኮ ዞን በጉራ ፈርዳ በአማራ ላይ አነጣጥሮ በተፈፀመው ጭፍጨፋ ቢያንስ 15 አማራዎች ተገድለዋል። 5)በተመሳሳይ በጉራ ፈርዳ ወረዳ አሮጌ ብርሀን በተባለ ቀበሌ ገጠር ላይ ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 5:00 ጀምሮ ቢያንስ ከ21 በላይ የአማራ ተወላጆች በጥይትና በድምፅ አልባ መሳሪያዎች በአሰቃቂ መልኩ ተገድለው አድረዋል፤ በርካቶች ቆስለዋል፤ ከፍተኛ ሀብት ንብረት ተዘርፏል፤ ወድሟል። 6)በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ጊንቢ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ መትረጊዬስና ሌሎች የቡድን መሳሪያዎችን በታጠቁ በግምት ቁጥራቸው 60 የሚሆኑ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ትናንት ጥቅምት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት አስገድደው በት/ቤት በሰበሰቧቸው አማራዎች ላይ የቦንብና በጥይት በፈፀሙት የጅምላ ጭፍጨፋ እስካሁን በደረሰን መረጃ ከ67 በላይ አማራዎች ተገድለዋል፤ ከ20 በላይ ቆስለዋል። ቁጥሩ ከዚህ በላይ ያሻቅባል! በአማራ ላይ በተለያዩ አካባቢዎች በተደጋጋሚ የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚፈፅሙምም ሆነ የሚያስፈፅሙ፣በፀረ አማራ አቋማቸው በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚተባበሩ፣የተሰጣቸውን መንግስታዊ ኃላፊነትን በተገቢነት ያልተወጡ ጠ/ሚ አብይ አህመድን ጨምሮ የጊዜ ጉዳይ እንጅ በዘር ማጥፋት ወንጀል ከመጠየቅ አያመልጡም። የአማራን ዘር ማጥፋት ይቁም! ፍትህ ለአገር ገንቢው ለባለ ገናና ታሪኩ የአማራ ህዝብ!

Source: Link to the Post

Leave a Reply