
በአማራ ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገው ስርዓታዊ የእስር መቻ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ስለመሆኑ ብዙዎች እየተናገሩ ነው፤ በደብረ ብርሃን እና በአዲስ አበባ ንፋስ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሁለት የመንግስት ሰራተኞች መታፈናቸው ተሰምቷል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 11/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በአማራ ላይ ማንነትን መሰረት ያደረገው ስርዓታዊ የእስር መቻ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ስለመሆኑ ብዙዎች እየተናገሩ ነው፤ ይህ አፈናን አብዝቶ የመለማመድ የኦህዴድ ብልጽግና አካሄድ በአስቸኳይ እንዲቆምም እየተጠየቀ ነው። በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ እና ቦሌ ክፍለ ከተማ ሁለት የመንግስት ሰራተኞች መታፈናቸው ተሰምቷል። አሻራ ሚዲያ ጋዜጠኛ ጌራ ጌታቸውን ዋቢ አድርጎ የሰራው ዘገባ እንዳመለከተው አበባው ማሙዬ የተባለ ትውልድ እና እድገቱ በሰሜን ሸዋ ዞን መርሃቤቴ አካባቢ የሆነ ወጣት በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ ዘጠኝ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ባለሙያ ሆኖ የሚሰራ ሲሆን ቤተሰብ ለመጠየቅ በሄደበት ሚያዚያ 30/2015 ዓ.ም በደብረ ብርሃን ከተማ መታፈኑ ታውቋል፡፡ በወቅቱ በደብረብርሃን ከተማ ጠባሴ ጅሩ መንገድ አካባቢ ከወንድሙ ጋር ሲንቀሳቀስ ሲቪል የለበሱ እና በመከላከያ ፓትሮል መኪና የሚንቀሳቀሱ ሰዎች ለጥያቄ እንፈልግሃለን ብለው የወሰዱት ሲሆን እስካሁን አድራሻው አልታወቀም። በተመሳሳይ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦሌ ቅርንጫፍ በባለሙያነት ተቀጥሮ ይሰራል የተባለው ጌታነህ ታከለ አበጀ ሚያዝያ 28/2015 በወረዳ 13 ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት በሁለት የፌደራል ፖሊሶች ቤቱ ከተፈተሸ በኋላ ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስዷል፤ ቤተሰብም ለከፍተኛ ጭንቀት መዳረጉ ተሰምቷል።
Source: Link to the Post