“በአማራ ላይ እየደረሰ ያለው እልቂት በአለም ላይ የታዩትን የጅምላ ፍጅት ባህርያትን ሙሉ በሙሉ ያሟላ በማያሻማ መልኩ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው” ሲሉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢ…

“በአማራ ላይ እየደረሰ ያለው እልቂት በአለም ላይ የታዩትን የጅምላ ፍጅት ባህርያትን ሙሉ በሙሉ ያሟላ በማያሻማ መልኩ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው” ሲሉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢ…

“በአማራ ላይ እየደረሰ ያለው እልቂት በአለም ላይ የታዩትን የጅምላ ፍጅት ባህርያትን ሙሉ በሙሉ ያሟላ በማያሻማ መልኩ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው” ሲሉ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አብርሃም ጌጡ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሞማ ታህሳስ 17 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአማራ ሚዲያ ማዕከል ከመላው የኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንትና የባልደራስ መኢአድ ቅንጅት የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ከሆኑት ከአቶ አብርሃም ጌጡ ጋር በመተከሉ ጅምላ ፍጅትና በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ቆይታ አድርጓል። አቶ አብርሃም ሲቀጥሉ የአማራ ህዝብ በኢትዮጵያ ባለፉት 45 ዓመታት ሴረኛው ሕወሓት በ1968 ደደቢት ላይ የጠነሰሰውን ማኒፌስቶውን፣መዋቅሩንና ስትራቴጅውን ተጠቅሞ በተቀናጀና በተጠናከረ መልኩ የአማራ ህዝብ የሌለበትን እዳ እንዲከፍል ስለማድረጉ አውስተዋል። የሰው ልጅ በዘሩ፣በብሄሩ፣በጎሳው፣ ቋንቋው፣በሀይማኖቱ ተለይቶና ተፈርጆ ሆንተብሎ ጥቃት የሚፈፀምበት ከሆነ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የዘር ፍጅት ተብሎ ነው የሚጠራው ሲሉም አክለዋል። በመሆኑም በአማራ ላይ እየደረሰ ያለው እልቂት በአለም ላይ የታዩትን የጅምላ ፍጅት ባህርያትን ሙሉ በሙሉ ያሟላ ነው ያሉት አቶ አብርሃም በማያሻማ መልኩ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈፀመበት ነው ብለዋል። በመተከል ቡለን ወረዳ ታህሳስ 13ለ14 የተፈፀመው እልቂት ሞትን፣ፍጅትን እንድንላመደው እያደረገ ያለ እጅግ አሳዛኝ ጭፍጨፋ መሆኑን የተናገሩት አቶ አብርሃም ለዚህም መንስኤው ምንም ዓይነት መነሻ በሌለው ሁኔታ ገደብ የሌለው አንድን ዘር ብቻ ትኩረትና ማዕከል ያደረገ ጥላቻ የወለደው ሀይል ያረቀቀው ህገ መንግስት ሞትንና ደምን፣ግድያንና መፈናቀልን እያስከተለ ስለመሆኑ ገልፀዋል። አቶ አብርሃም የፍጅቱን አሳሳቢነት ሲገልፁም የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ መተከል ለስብሰባ ሄደው ከመመለሳቸው የጅምላ ፍጅቱ መፈፀሙ ሁኔታውን አሳሳቢ እንደሚያደርገው ነው የገለፁት። የጂኦፖለቲካ ጉዳይ፣ፅንፈኛና አሸባሪ የሆኑት ሕወሓትና ኦነግ ሸኔ ፍላጎት፣በመንግስት መዋቅር ውስጥ በተሰገሰጉ ተባባሪ ሀይሎች በሚቀርብላቸው ስንቅና ትጥቅ የሚንቀሳቀሱና የሕወሓትን ጡት ጠብተው ያደጉ ወራሾች፣ከውጭ ግድቡ ቢጠናቀቅ ጥቅማችን ይነካል ብለው በሚያስቡና በሚታገሉ በቋሚነት ግብፅና በተለዋዋጭነት ሱዳን በመተባበር የመተከል ቀጠናን እያተራመሱት መሆኑን ገልፀዋል። በመተከልም ሆነ በኦሮሚያ ወለጋና በሌሎችም አካባቢዎች በተደጋጋሚ ከሚፈፀመው አማራ ተኮር ፍጅት በስተጀርባ ለመስፋፋት የሚያስቡና የሚንቀሳቀሱ ህልመኞች በጥላቻ ታውረው በጠላትነት የፈረጁትን የአማራን ህዝብ ለማጥቃት አደረጃጀታቸውን ቀይረው የመምጣታቸው ነገር በግልፅ እንደሚታይም ተጠቁሟል። አቶ አብርሃም በመተከሉ እልቂት የመንግስት ሀይሎች በቀጥታም ሆነ በስውር እጃቸው እንዳለበት ለማሳያነት ካነሱት ጉዳይ መካከልም በአንድ ወቅት ም/ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን መተከል ላይ የሚፈፀመውን እልቂት ለማስቆም አማራጩ በየጊዜው ያለማንም ሀይ ባይ በጅምላ እየተጨፈጨፈ ያለው አማራ ራሱን መከላከል እንዳለበት በመናገራቸው ከተለያዩ አቅጣጫዎች የተከፈተባቸው ዘመቻ ይታወሳል ብለዋል። በጥቅሉ የመተከል ጭፍጨፋ መንግስት በሀሳብና በሎጅስቲክ የሚደግፈው፣ታቅዶበትና ታስቦበት እየተፈፀመ ስለመሆኑ ብዙ ማሳያዎች ስለመኖራቸው አስታውቀዋል። አለም የእኛ እልቂት ስለሆነ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ዝምታን መርጧል ያሉት አቶ አብርሀም ትሕነግ በማይካድራ አማራ ላይ በፈፀመው ፍጅት ስናዝን በመተከል በየቀኑ እየተደጋገመ ነው፤አንድ ቀን ግን ወንጀለኞች በፍትህ አደባባይ መቆም አይቀርላቸውም ሲሉ ተደምጠዋል። ከመተከል አማራውን ማፅዳት ለምን አስፈለገ ሲሉ የጠየቁት አቶ አብርሃም ሕወሓት በመከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ነገ ወደ አራት ኪሎ እየገሰገሰ መሆኑን የተገነዘበው መንግስት የወሰደውን እርምጃ በመተከል ላይ መውሰድ አለበት ብለዋል። ለሀገራዊ ምስቅልቅሉ መፍትሄዎችን የጠቆሙት አቶ አብርሃም እንደ መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ መንግስት ከወታደራዊ ድሉ ባሻገር የፖለቲካ ሀይሎች ቅርርብና ተግባቦት እንዲፈጠር ፍቃደኝነቱና ለተግባራዊነቱም ቁርጠኝነት ሊኖረው ይገባል ብለዋል። መንግስት በሰላሙ፣በፀጥታውና በዲፕሎማሲው ረገድም ትልቅ ስራ ማከናወን እንደሚጠበቅበት፣ በተከፈለው መስዋዕትነትም ከጨቋኙ ሕወሓት ነጻ የወጡትን የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ ነዋሪዎችን ጥያቄ መመለስ፣የህግ የበላይነትን በማስከበር ወንጀለኞችን ይዞ ለፍትህ አደባባይ ማቅረብ አስፈላጊ ነው ብሎ መኢአድ እንደሚያምንና ለተግባራዊነቱም እንደሚሰራ ነው አቶ አብርሃም ያስረዱት። ከአቶ አብርሃም ጌጡ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ/AMC የዩቱብ ገጽ ላይ የምናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply