በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ባለው የዘር ማጥፉት ወንጀል መራሹ የኦህዴድ ብልፅግና መንግስት ግንባር ቀደም ተጠያቂ ነው ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ…

በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ባለው የዘር ማጥፉት ወንጀል መራሹ የኦህዴድ ብልፅግና መንግስት ግንባር ቀደም ተጠያቂ ነው ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ…

በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ባለው የዘር ማጥፉት ወንጀል መራሹ የኦህዴድ ብልፅግና መንግስት ግንባር ቀደም ተጠያቂ ነው ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) በ22/02/2013 ዓ.ም ምሽት ላይ በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ጋንቃ ቀበሌ ከ200 በላይ አማሮች በማንነታቸው ብቻ ተለይተው በጅምላ በተፈፀመባቸው የዘር ማጥፋት ድርጊት የተሰማውን መሪር ኃዘን ይገልፃል ነው ያለው። ላለፉት ሰላሳ አመታት በሀገሪቱ ውስጥ በአማራ ህዝብ ላይ ማንነትን መሠረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋና የዘር የማፅዳት ወንጀል እየተፈፀመ መቆየቱን መኢአድ አውስቷል። በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በአማራው ህዝብ ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ ማስቆም የሚችል የመንግስት ሀይል አለመኖሩ ደግሞ ችግሩን እያባባሰው መጥቶ ዛሬ ላይ የአማራ ህዝብ ከፍተኛ የህልውና አደጋ ተጋርጦበት ይገኛል ሲልም አክሏል። በዚህም ምክንያት በእነዚህ በርካታ ዓመታት በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል ዛሬም ተባብሶ ስለመቀጠሉ የገለፀው መኢአድ መንግስትም በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን ተደጋጋሚ የዘር ማጥፋት ወንጀል በስሙ ከመጥራትና ብሔራዊ የደኅንነት ስጋት አድርጎ ጥቃቱን ከማስቆምና የችግሩን ፈጣሪዎች በቅጡ ለይቶ የሚመጥን እርምጃ በወቅቱ ከመውሰድና የህዝቡን ደህንነት ከመጠበቅ ይልቅ እሹሩሩ በማለትና ወንጀሉን በማድበስበስ የወንጀሉ ቀንደኛ ተባባሪ ሆኖ ይገኛል ነው ያለው። በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የሚንቀሳቀሰው ታጣቂው የኦነግ ሸኔ ሀይል ከኤርትራ ሙሉ ትጥቅ ይዞ እንዲገባ በማድረግ በየቦታው ካሉ አማራ ጠል ፅንፈኛ ሀይሎች ጋር በቅንጅት አማራዉን ማኅበራዊ ረፍት ለመንሳትና በጅምላ ለመጨፍጨፍ እንዲችሉ ፍቃድ የሰጣቸው የፌደራል መንግስቱ ነው ብሎ እንደሚያምንም ጠቅሷል። በኦህዴድ መራሹ የብልፅግና መንግስት የስልጣን መዋቅር ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ አፍቃሪ ኦነግ የኦህዴድ ባለስልጣናት በአካባቢው የነበረውን የኦሮሚያ ልዩ ሀይል በማስወጣትና ድርጊቱ ሲፈፀም እየሠሙና እያወቁ እንዳላዩ ማለፋቸው የዚህ የወንጀል ድርጊት ተሳታፊ እንደሆኑ ይቆጠራል ሲልም አክሏል። በአጠቃላይ የአማራ ሕዝብ የዘር ማጥፋት ታውጆበት እያለ የማዕከላዊ መንግስቱ ዝምታና እንዳላየ ማለፉ እጅግ አሳፋሪ ተግባር ነው ያለው የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት የአማራው ሕዝብ በመንግስት ድጋፍ እየተፈፀመበት ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ተደራጅቶ እና ተዘጋጅቶ እንዲመክት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) ጥሪውን እያቀረበ በአሸባሪው የኦነግ ሽኔ ሽፍታ ቡድን ህይዎታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መፅናናትን እንዲሰጥልን እንመኛለን ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply