በአማራ ክልል ለሚገኙ የአይን ሞራ ግርዶሽ እና የአይን ቆብ መቀልበስ ችግር ላለባቸው ህሙማን በነጻ የቀዶ ጥገናና ተያያዥ የአይን ህክምና አገልግሎቶችን እየሰጠ መሆኑን የጎንደር ዩኒቨርስቲ አ…

በአማራ ክልል ለሚገኙ የአይን ሞራ ግርዶሽ እና የአይን ቆብ መቀልበስ ችግር ላለባቸው ህሙማን በነጻ የቀዶ ጥገናና ተያያዥ የአይን ህክምና አገልግሎቶችን እየሰጠ መሆኑን የጎንደር ዩኒቨርስቲ አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዓይን ህክምናና ማሰልጠኛ ማዕከል ከአጋር ድርጅቶች ጋር ባለው ፕሮጀክት ስምምነት መሰረት በአማራ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር የነጻ የአይን ህክምና ዘመቻ ለበርካታ ዓመታት ሲያከናውን መቆየቱን ጠቅሷል፡፡ ይሁን እንጅ የነጻ ህክምና ዘመቻ አገልግሎቱ በኮቪድ-19 ምክንያት ለተወሰኑ ወራት ተቋርጦ መቆየቱን ያወሳው የህክምና ክፍሉ የወቅቱን ችግር ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ከጥቅምት 1/2013 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30/2013 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የአይን ህክምና በነጻ ለህብረተሰቡ በመስጠት ላይ ይገኛል ብሏል፡፡ በመጨረሻም ህክምናው በዋናነት ትኩረት የሚያደርገው የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና፣ የአይን ቆብ መቀልበስ ቀዶ ጥገናና ተያያዥ የአይን ህክምናዎች በመሆኑ፣ ማንኛውም የዓይን ችግር ያለበት የክልሉ ማህበረሰብ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል በመገኘት የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆን ሲል ማዕከሉ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply