በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ በመንግስት ፀጥታ አካላት የተወሰደውን እርምጃ አምስቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት አወገዘ፡፡በአማራ ክልል እየተከናወነ የሚገኘው ግጭት እና ለአራት ወራት እንዲቀጥል…

በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ በመንግስት ፀጥታ አካላት የተወሰደውን እርምጃ አምስቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት አወገዘ፡፡

በአማራ ክልል እየተከናወነ የሚገኘው ግጭት እና ለአራት ወራት እንዲቀጥል የተወሰነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመጨረሻ ግብ የክልሉን ኗሪ ሰቆቃ ማርዘምና ያለ ጠያቂ ሕዝቡ ላይ የሚደርሰውን መከራ ማስቀጠል ነው ሲሉም ፓርቲዎቹ ኮንነውታል፡፡

በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መኢአድ፣ ኢሕአፓ፣ አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ አማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና እናት ፓርቲ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም አገራችን ካለችበት ውስብስብ ፖለቲካዊ ችግሮች አኳያ ጦርነትና አስቸኳይ ጊዜ አዋጆች መፍትሔ አያመጡም ብለዋል፡፡

ፓርቲዎቹ በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ በግጭቱ ተሳትፎ ያልነበራቸው ከ51 በላይ ንጹሐን ዜጎች በመንግሥት ወታደሮች መገደላቸውን ከአካባቢው ነዋሪዎችና የዓይን እማኞች መረዳት ችለናል ብለዋል ።

በመሆኑም ይህን ድርጊት በፈፀሙ የፀጥታ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል፡፡

አምስቱ ፓርቲዎች 3 የአቋም መግለጫ ያወጡ ሲሆን መንግስት በክልሉ እያደረገ ያለውን ግጭት እንዲያቋም፣በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ በግፍ ለተገደሉ ዜጎች ተጠያቂነት እንዲያሰፍን እና የአስቸኳይ ግዜ ማራዘም ክልሉን ማፈራረስ በመሆኑ ከዚህ ድርጊቱ መንግስት እንዲቆጠብ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አቤል ደጄኔ
ጥር 29 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply