በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ በነበረው ግጭት ከ80 በላይ በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አስታወቀበአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን መር…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/d50-UPF_Q7ukIUe-JdGhJbOWcv3Cbdtg884RiZdKLX1mHwJ3J41iB2Cld-ASoYSR8kmLa5rT1XfbpIYQfrUO4qdkjJpVAVJA-c4fF_gSpYZKeI--6F6ZLDE3w0DytZW1XE5j_Hram9FeMm0AziLLM1WgJxEHjNjmdqdcCdvgwgCdZlN5QGwFFdQUHjbtZgV_lCsThIWuZL2JGJfSDAVv6xy2UcFzjQHXEaL1Kbh52K0rVYlno9p3aKZyhu14wosx61_y7dxuVrB0WI5E8m_lUAzuphcDRTB9G1P4gkKOXfyT7fqqgRd8j2RtipjCGzinJRMwTS2n7luLC97gPWhAkA.jpg

በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ በነበረው ግጭት ከ80 በላይ በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አስታወቀ

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኖች መካከል በነበረ ግጭት ከ80 (ሰማንያ) በላይ የሆኑ በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ከግድያው በተጨማሪ የአካል ጉዳት፣ ድበደባ፣ ማስፈራራትና ሌሎችም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ተፈጽመዋል ብሏል።

ለግድያው ዋነኛ ምክንያት በግጭቱ ወቅት የነበረው ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ መሆኑን የጠቆመው ኢሰመጉ በተጨማሪም ቤት ለቤት በመዘዋወር ግድያ መፈጸሙን ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት መቻሉን ጠቁሟል።

የተፈጸሙትን ግድያዎች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በአካል በመገኘት ምርመራ በማድረግ ለማረጋገጥ አለመቻሉን አመላክቷል።

በክልሉ በግጭቱ ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ አካላት በግጭቱ ተሳትፎ የሌላቸውን ሰዎች ላይ የጅምላ ግድያ ከመፈጸም እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርቧል።

ጥር 29 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply