You are currently viewing በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት ከተማ ያለፉትን ቀናት በአሸባሪው ሸኔ አማካይነት እየተፈፀ ያለው ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር አስታወቀ! ጥር 17 ቀ…

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት ከተማ ያለፉትን ቀናት በአሸባሪው ሸኔ አማካይነት እየተፈፀ ያለው ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር አስታወቀ! ጥር 17 ቀ…

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት ከተማ ያለፉትን ቀናት በአሸባሪው ሸኔ አማካይነት እየተፈፀ ያለው ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር አስታወቀ! ጥር 17 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ጥቃት አድራሾቹ በተደራጀ መልክ የሚንቀሳቅሱ እና ግዙፍ የጦር መሳሪያዎችን የታጠቁ መሆናቸዉን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ተስፋዬ መንግስቱ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል። መንግስት ባሰማራቸው የፀጥታ ሀይሎች ላይ ሳይቀር ጥቃቱን እንደሚፈፅሙ ያነሱት ኃላፊው ተጨማሪ የፀጥታ ሀይሎች ወደ ሥፍራው እንዲሰማሩ የማድረግ ጥረት ቢኖርም ለቡድኑ ቀድሞ መረጃ የሚሰጡ አካላት በመኖራቸዉ የፀጥታ ሀይሎች ሥፍራው ላይ ሲደርሱ ጥቃት አድራሾቹ እንደሚሸሹ ገልጸዋል። በዚህ ሂደት አሳቻ ሰዓት እየጠበቁ ጥቃት ማድረሳቸውን አላቆሙሙ ያሉት ተስፋዬ ንፁሀን እና ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች የጥቃቱ ሰለባ እየሆኑ እንደሚገኙም ተናግረዋል፡፡ በከተማዋ በአሁን ሰዓት አንፃራዊ መረጋጋት ያለ እና የተኩስ ልውውጡም የተገታ ቢመስልም ጥቃት አድራሾቹ አመቺ ጊዜ ጠብቀው ማጥቃት እንደማያቆሙ ገልጸዋል። በከተማዋ ያለው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ያነሱት ከንቲባው የደረሰውን የጉዳት መጠን ለማወቅ አስተዳደሩ መቸገሩን ተናግረዋል፡፡ የፀጥታ መደፍረሱ ከአቅም በላይ መሆኑንም በመግለጽ፤ መንግስት ቋሚ እልባት በመስጠት በተደራጀ እና በተቀናጀ መልኩ ኃይል እንዲያሰማራም ከንቲባው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply