
የአማራ ክልል ባለሥልጣናት በክልሉ ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር በሚል ባካሄዱት ዘመቻ ከ4500 በላይ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ አሳውቀዋል። ከአንድ ሳምንት በፊት የተጀመረው ይህ ዘመቻ ከአወዛጋቢው በግለሰቦች እጅ ያሉ የጦር መሳሪያዎችን ከመመዝገብ ጋር ነበር አብሮ የተካሄደው። ይህን ዘመቻ ተከትሎ በአንዳንድ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ ተቃውሞ ምክንያት በተከሰተ ግጭት ችግር አጋጥሞ እንደነበር ተዘግቧል።
Source: Link to the Post