በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ጃራ መጠለያ የተጠለሉ ዜጎች በከባድ ረሃብ ላይ እንገኛለን ብለዋል

በሰሜን ወሎ ዞን በሃርቡ ወረዳ በጃራ መጠለያ በጊዜያዊነት ተጠልለው የሚገኙ ዜጎች በከፍተኛ የምግብ እጥረት ችግር ውስጥ ነን ሲሉ ለጣቢያችን ተናግረዋል ።

ተፈናቃይ ዜጎቹ ለሁለት ወር ያክል በተደጋጋሚ የምግብ እርዳታ ለማግኘት መንግስትን ብንጠይቅም ለችግራችን መፍትሔ የተሰጠ አካል የለም ብለዋል።

በጃራ መጠለያ ጣቢያ 1 ሺህ 3 መቶ ቤተሰቦች እንደሚገኙም ነግረውናል።

ተፈናቃዮች፣ ከምዕራብና ምስራቅ ወለጋ እንዲሁም ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ ናቸው።

ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት ከምግብ እጥረት በተጨማሪ በአፋር ታጣቂ ቡዱኖች ጥቃት እየደረሰበ ነው ብለዋል።

ልዑል ወልዴ

የካቲት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply