በአማራ ክልል በባለፈው ዓመት ብቻ 1 ሺህ 700 ሕፃናት ያለ እድሜያቸው ተድረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ብሔራዊ ክልል በ…

በአማራ ክልል በባለፈው ዓመት ብቻ 1 ሺህ 700 ሕፃናት ያለ እድሜያቸው ተድረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራ ብሔራዊ ክልል በ2012 ዓ.ም ከ1 ሺህ 700 በላይ የልጅነት ጋብቻዎች መፈጸማቸውን የክልሉ ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የሴቶች ንቅናቄና ተሳትፎ ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ስማቸው ዳኜ ለቢቢሲ ገለፁ። በአማራ ክልል የልጅነት ጋብቻ በስፋት የሚፈጸም መሆኑን ለቢቢሲ የገለጹት አቶ ስማቸው ዳኜ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ቁጥሩ ይበልጥ እንዲጨምር ማድረጉን አስረድተዋል። ይህ መረጃ የተገኘው ስለጉዳዩ የሚቆረቆሩ ሰዎች በሚሰጡት መረጃ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ፣ የተጠናከረ የመረጃ ስርዓት ስለሌለ ቁጥሩ ይህ ብቻ ነው ለማለት ያስችግራል ብለዋል። አብዛኛው የልጅነት ጋብቻ የህግ ተጠያቂነትን ለመሸሽ በድብቅ የሚፈጸም መሆኑን የሚናገሩት ኃላፊው በዚህ ምክንያት ይፋ ሳይደረግ የሚቀር እንዳለም ጠቁመዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህጻናት መርጃ ድርጅት /ዩኒሴፍ/ እኤአ 2019 ባደረገው ጥናት መሠረት በኢትዮጵያ የልጅነት ጋብቻ በስፋት ከሚታይበቸው 50 ወረዳዎች ውስጥ 23ቱ በአማራ ክልል ይገኛሉ። እንደጥናቱ ከሆነ የልጅነት ጋብቻ ምጣኔ ሃብታዊ ተጽዕኖው ብቻ ቢታይ እንኳን የልጅነት ጋብቻ በማስቀረት 1.5 በመቶ ዓመታዊ የገቢ ጭማሪ ማግኘት ይቻላል። በትምህርት ረገድ ከታየ ደግሞ የልጅነት ጋብቻውን በማስቀረት ልጆቹ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ቢያጠናቅቁ በሃገር ኢኮኖሚ ውስጥ ከ10-20 በመቶ ሚና ይኖራቸዋል። ሁለተኛ ደረጃን ካጠናቀቁ ደግሞ 15-25 በመቶ ከፍ ይላል። ይህ ደግሞ በየዓመቱ 646 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ የሚጨምር ነው ተብሏል ሲል የዘገበው ቢቢሲ አማርኛ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply