You are currently viewing በአማራ ክልል በተመረጡ የተለያዩ ከተሞች የብልጽግናን ጸረ አማራ አገዛዝ የሚያወግዙ የተቃውሞ ሰልፎች ተደርገዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   መጋቢት 25 ቀን 2015 ዓ/ም…

በአማራ ክልል በተመረጡ የተለያዩ ከተሞች የብልጽግናን ጸረ አማራ አገዛዝ የሚያወግዙ የተቃውሞ ሰልፎች ተደርገዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 25 ቀን 2015 ዓ/ም…

በአማራ ክልል በተመረጡ የተለያዩ ከተሞች የብልጽግናን ጸረ አማራ አገዛዝ የሚያወግዙ የተቃውሞ ሰልፎች ተደርገዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 25 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በህወሓት መራሹ ዘመን ባለፉት 27 ዓመታት በአማራ ህዝብ ላይ የተፈጸመው የጅምላ ፍጅት፣ እስር፣ መፈናቀል እና ስደት፣ ከ2013 ጀምሮ የፈጸመው የዙር ወረራ እና ፍጅትም የሚረሳ አይደለም። መጋቢት 24/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ሰፊው የአማራ ህዝብም እየደረሰበት ያለው ተደጋጋሚ እልቂት እና መፈናቀል ከህወሓት አገዛዝ በእጅጉ በባሰ መልኩ ተጠናክሮ መቀጠሉ የሚታወቅ ነው። መጋቢት 24/2010 የጠቅላይ ሚኒስትረጀ ብሎም የብልጽና አገዛዝ መምጣቱ ለአማራው ብሎም ለኢትዮጵያ ህዝብ ይዞት የመጣው ቱሩት ሳይሆን የመከራ ቀንበርን፣ እልቂት እና መፈናቀልን ነው በሚል በደም ላይ በመቆም ከሚደረግ የድጋፍ ሰልፍ በተቃራኒው ከእውነት ጋር በመቆም ጠ/ሚኒስትሩን እና የስርዓታቸውን ደባ የሚያጋልጥ የተቃውሞ ሰልፍ በአማራ ክልል በተመረጡ የተለያዩ ከተሞች ተደርጓል። በህዝብ አስተባባሪ ኮሚቴ በኩል በተደረገ ጥሪ አማካኝነት በአማራ ክልል በተመረጡ የተለያዩ ከተሞች ከተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች መካከልም በስኬት የተጠናቀቁ በሚል የተገለጹት እንደአብነት:_ 1) መርዓዊ፣ 2) ኮረም፣ 3) ምንጃር አረርቲ፣ 4) በሀብሩ ወረዳ መርሳ እና ውርጌሳ፣ 5) ቆቦ፣ 6) መቄት፣ 7) ጅጋ፣ 8 ቡሬ እና 9) ደምበጫ የተባሉ አካባቢዎች ይገኙበታል። በሰላማዊ ሰልፉም እነ አርበኛ ዘመነ ካሴ፣ እነ ፖለቲከኛ ስንታዬሁ ቸኮል፣ እነ ጋዜጠኛ እና የታሪክ ጸሀፊ ታዲዎስ ታንቱ፣ ጋዜጠኞች፣ በእስር ላይ ያሉ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ፋኖዎች እና ሌሎች ፍትህ ፈላጊ ወገኖች ሁሉ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ተጠይቋል። የአማራ ልዩ ኃይል ትጥቅ እንዲፈታ እና እንዲበተን ወይም ወደ ሌላ መዋቅር እንዲካተት የሚለው የስርዓቱ ውሳኔም ክፉኛ ተቃውሞ ገጥሞታል። የአማራ ህዝብ የህልውና አደጋ ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት የልዩ ኃይል መዋቅሩ ይፍረስ ማለትም ለተጨማሪ እልቂት ድግስ ማዘጋጀት እንደማለት ስለመሆኑም ተገልጧል። በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ፍጅት፣ መፈናቀል፣ መሳደድ እና ቤት ፈረሳ በአስቸኳይ እንዲቆምም ተጠይቋል። ከወልቃይት፣ ጠገዴ፣ጠለምት እና ራያ መከላከያ ሰራዊት በሴራ እንዲወጣ መደረጉ እንዲቆም እንዲሁም የወልቃይት፣ጠገዴ፣ጠለምት፣የራያ፣ በጎጃም የመተከል እና በሸዋ የደራ አማራ ማንነት እና ሌሎችም ጥያቄዎች እንዲመለሱ ተጠይቋል። በዘር ፍጅት ወንጀል ተጠያቂ ሊሆኑ የሚገባቸውን አቦይ ስብሃት ነጋን ለህክምና አሜሪካ እንዲሄዱ ፈቅዶ የሀገር ባለውለታ የሆኑትን የጦር ጄኔራል ተፈራ ማሞን ህክምና መከልከል ክህደት እና ጸረ አማራነት ነው፤ በአስቸኳይ በፈለጉት ቦታ ህክምና የማግኘት መብታቸው ሊከበር ይገባል የሚል ጥሪም ቀርቧል። በተመሳሳይ በባህር ዳር ከተማም የተቃውሞ ሰልፉ የተደረገ ቢሆንም በመሃል አድማ በታኞች በሰልፈኞች ላይ ድብደባ በመፈጸም እንዲበተን አድርገዋል። በደብረ ታቦር ቀድሞ ከፍተኛ የጸጥታ አካላት ስምሪት በመደረጉ እና የመስተዳድር አካላትም ሰልፉ እንዳይደረግ ከመከልከል አልፈው ቢያንስ ከአስር በላይ ወጣቶችን ማሰራቸው፣ በወልድያ ደግሞ የሰልፉ አስተባባሪዎች ከጸጥታ አካላት ጋር በመምከር ለሌላ ጊዜ እንዲራዘም ማድረጋቸውን ነው የአሚማ ምንጮች የገለጹት።

Source: Link to the Post

Leave a Reply