በአማራ ክልል በተደጋጋሚ እየተወሰደ ያለው የበቀል እርምጃ በኦሮሚያ ክልልም እንዲፈጸም ሊፈቀድ አይገባም—እናት ፓርቲ በአማራ ክልል በተደጋጋሚ እየተወሰደ ያለው የበቀል እርምጃ በኦሮሚያ ክ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/kFwMiM5nuDHGRmsLxdVdsaJe9X-qu58-EerYoqV9oBzT3G4ShNXhmlYGK6vUz653JmejoPaXt7HYePx7wWV4JlUqeH6iWlpdWxpLHIm1cuN-cTleckavWOFBeEp1Q06FDkTdf9NWfGn4jOLG6MwnCmK5rfRTd2a3KwvDnbRHrS3iiAmkmR7ML2EpaFnlZ5vTHmm9BWi9tN2e-NvZWZmw-3PG5ZMXFcy9xNLOVxtYqupfGCYknlpl9iyOoeF6Ora29QR0VQvZN2jQMJGU_qQ21BV8ft2RUXMK_1WV8b6VmLqrpaRvUauQnW9LD_pL8VZwXCHGMaX_e3fHQeFmcKu-Rw.jpg

በአማራ ክልል በተደጋጋሚ እየተወሰደ ያለው የበቀል እርምጃ በኦሮሚያ ክልልም እንዲፈጸም ሊፈቀድ አይገባም—እናት ፓርቲ

በአማራ ክልል በተደጋጋሚ እየተወሰደ ያለው የበቀል እርምጃ በኦሮሚያ ክልልም እንዲፈጸም ሊፈቀድ አይገባም ሲል እናት ፓርቲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ዓርብ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ላይ ያልታወቁ ሰዎች በመከላከያ ሠራዊት አባል ላይ የፈጸሙትን ግድያ ተከትሎ የመንግሥት ወታደሮች የበቀል እርምጃ መውሰዳቸው ተገልፃል፡፡

በዚህም በቀበሌው አርሶ አደሮች ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ መፈጸማቸውን ፓርቲያችን ከአካባቢው ነዋሪዎች ለመረዳት ችሏል ሲል በመግለጫው አመላክቷል።
በተጨማሪም ሶስት ሰዎች እስካሁን የት እንደደረሱ አለመታወቁንም ለመረዳት አለመቻሉን ፓርቲው ገልፃል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የቀበሌው አርሶ አደሮች መንግሥት “ኦነግ ሸኔ” እያለ ከሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ራሳቸውን ለመከላከል በመንግሥት ተመዝግቦ የታጠቁትን የነፍስ ወከፍ መሣሪያ የመከላከያ ሠራዊት በቤት ለቤት አሰሳ እንደወሰደባቸውና ይህ ደግሞ ለከፍተኛ የአደጋ ተጋላጭነት እንደዳረጋቸው አስረድተዋል ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ እናት ፓርቲ በመከላከያ ሠራዊት አባል ላይ የተፈጸመውን ግድያ በከፍተኛ ሁኔታ ያወግዛል ሲል ገልፃል።

የመከላከያ ሠራዊት አባል ግድያን ተከትሎ የመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች የፈጸሙት የጅምላ ጭፍጨፋ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጸመ ያለው የበቀል እርምጃን ወደ ኦሮሚያ ክልል የማዛመት ሥራ በመሆኑ በጽኑ ያወግዛል ብሏል፡፡

በአቤል ደጀኔ
መጋቢት 10 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply